FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, December 26, 2012

የሶሪያ ፖሊስ ሠራዊት አዛዥ የፕሬዚዳንት አል-አሳድን መንግስት ከዱ


ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የሶሪያ ፖሊስ ሠራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብዱልአዚዝ አልሻላል የፕሪዚዳንት አል አሳድን መንግስት በመክዳት ወደ ቱርክ መኮብለላቸውን ቢቢሲ ዘገበ።
የፖሊስ አዛዡ ከቱርክ ሆነው በለቀቁት የቪዲዮ ምስል ላለፉት ለተነሳበት ተቃውሞ ለዓመታት  መፍትሄ መስጠት ተስኖት አገሪቱን ወደ እርስበርስ እልቂት ያመራትን የፕሬዚዳንት አልአሳድን መንግስት መክዳታቸውን በግልጽ አስታውቀዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ሌተናል ጄነራል አብዱል አዚዝ መንግስትን በመክዳት ከሶሪያ አብዮተኞች ጋር ከተቀላቀሉት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት አንዱ ሆነዋል።
ጄነራሉ  መንግስትን ለመክዳት የወሰኑት <<ራካ >>በተሰኘችው ሰሜናዊ ያገሪቱ ግዛት ላይ የመንግስት ጦር ሰሞኑን የወሰደውን መጠነ ሰፊ የሀይል ጥቃት ተከትሎ ነው።
ጀነራል ሻላል በዚሁ መግለጫቸው ሠራዊታቸው የሶሪያውያንን ደህንነት በመታደግ ፋንታ በየደረሰባቸው ከተሞችና እና መንደሮች የጅምላ ጭፍጨፋ እየፈፀመ መሆኑ ፤ መንግስትን በመክዳት ከአብዮተኞቹ ጎን ይቆሙ ዘንድ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል።
<<ከሶሪያ ሠራዊት መክዳቴን በግልጽ አውጃለሁ። ምክንያቱም ሠራዊቱ የተሸከመውን የሶሪያ ህዝብን ከጥቃት የመከላከል ተልዕኮ በመዘንጋት በአንፃሩ በሶሪያውያን ላይ መጠነ-ሰፊ እልቂት እየፈጠረ ነው>> ሲሉም ተደምጠዋል-ጀነራል-አብዱልአዚዝ ሻላል።
በሶሪያ አብዮተኞች ያነሱትን የለውጥ ጥያቄ ተከትሎ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዘለቀው ግጭት 40 ሺህ ሶሪያውያን እንደሞቱ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment