FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, December 29, 2012

በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ


ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልግም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
ሳጅን ሽታየ በእለቱ ያጋጠመውን ድርጊት በዝርዝር አስረድቷል ።
ሳጅን ሽታየ ራሱን ለማጥፋት የወሰነው በእርሱ እና በቤተሰቡ ላይ የደረሰበት በደል ከሚችለው በላይ ሆኖበት መሆኑን ለኢሳት ተናግሯል ምናልባት ህይወትህን ብታጠፋ መንግስት የአእምሮ በሽተኛ ነህ ሊልህ ይችላልና አእምሮ በሽተኛ ነህ ወይ ተብሎ ለቀረበት ጥያቄ፣ ሙሉ ጤነኛ ሆኖማ ስራውን ችግሩ እስከተፈጠረበት ድረስ ሲሰራ እንደነበር ገልጿል፡፡
የኢሳት ባልደረቦች ሳጅን ሽታየ ራሱን እንዳያጠፋ ለረጅም ሰአት ምክር የለገሱት ሲሆን፣ በመጨረሻም እጁን ለፖሊስ በመስጠት ወደ ዞኑ እስርቤት ተወስዷል።
ረዳት ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሎማ ዲሣ አካባቢ የዲሣን ወረዳ ጥያቄ የሚያንቀሳቅሱ ሦስት ግለሰቦችን እንዲያስር ከዳዉሮ ዞን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት መመሪያ ተሰጥቶት ያለ ጥፋት ሰዉ አይታሰርም በማለቱም በዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ቅሬታ እንደተያዘበት ታውቋል።
የዲሣን ወረዳ ጥያቄ ያንቀሳቅሳሉና መታሰር አለባቸዉ ተብለዉ ከዞኑ ፖለቲካ ሀላፊ ከአቶ ሽመልስ ትዕዛዝ ከተላለፈባቸዉ ግለሰቦች መካከል አቶ አባቴ አሰፋ ፤ አቶ መስፍን ማሞ ፤ እና አቶ ደስታ ቶልባ ይገኙበታል።
በዳዉሮ ዞን የወረዳና ተያያዥ የመብት ጉዳዮች ገፈፋ ጋር በተያያዘ ከመምህር የኔሰዉ ገብሬ ራሱን በቤኒዚን ከማጋየት በኋላ ዓመት ባልተቆጠረ ጊዜ ዉስጥ ከ6 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን በዛፍ ላይ በመስቀል እና ከገደል ላይ በመወርወር ሞተዋል።

No comments:

Post a Comment