FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 28, 2012

በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የቀረበ ጥሪ !


የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሚባለውን የወያኔ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ መንግስት የተሾመ ለወያኔ ማፊያ ቡደን የሚያገለግል እንደሆነ በረጅም አመት የማጭበርበር የስራ ልምዱ አስመስክሯል ። ይህ ድርጅት ገለልተኛ እንዳልሆነ እየታወቀ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 34 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወያኔን በማይገባው ቋንቋ በሰላማዊ ትግል ታግሎ ወያኔን ለማስወገድ ውጤታማ ያልሆነ ልፋት እየለፉ ይገኛሉ ።
እነዚህ የተሰባሰቡት ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚከተሉት ሰላማዊ ትግል በጣም ዘመናዊ እና የሚዎደድ ቢሆንም ወያኔን የመሰለ ዘረኛ እና የተደራጁ የማፊያ ቡድኖችን ከስልጣን ለማስወገድ ትክክለኛ አካሄድ አይመስልም ። እነዚህ ድርጅቶች በ አሁኑ ሰአት በወያኔዎች የሚመራው የምርጫ ቦርድ መፍትሄ እንደማይሰጣችው እየታወቀ ለዚህ ድርጅት ጥያቄ ማቅረብ ጊዜን ከማባከን በተጨማሪ አምባገነኑን የወያኔ መንግስት በስልጣን ላይ እንዲቆይ እድሜውን ለማራዘም እድል እንደመስጠት ይቆጠራል።
እነዚህ የወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው አድለዎ ፣ አፈና ፣ዘረኛነት እና አምባገነናዊ አገዛዝን በመቃዎም ብሎም የሃገራችን ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን በወያኔ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ወይም ምርጫ ቦርድ እያደረሰባቸው ያለውን ጫና መቋቋም ከማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ ።
እነዚህ የምርጫ ቦርድን ጥያቄ ለመጠየቅ የተሰባሰቡ እና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ስብስብ የኢትዮጵያ ህዝብን የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ባላችው አቅም እየታገሉ ይገኛሉ ። ነገር ግን ገዡ ቡድን ከአምባገነንነቱ የተነሳ ተቃዋሚዎች  ህዝብን እንኳን ሰብስበው ማወያየት የማይችሉበት ደረጃ አድርሷቸዋል ።
ስለዚህ ተቃዋሚዎች እንታገልለታለን የሚሉትን የኢትዮጵያ ህዝብን ማወያየት እንኳን በማይችሉበት ሁኔታ፤ የገዡ መደብ ባስቀመጠላቸው አቤቱታ የማቅረብ መብት ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከመታገል ይልቅ ፤ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለመብቱ እንዲታገል አስቸኳይ ጥሪ ማቅረብ እና ህዝባዊ ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን መምራት አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው ።
የምትጠሩትን ህዝባዊ እና ሰላማዊ የትግል ጥሪ የኢትዮጵያ ህዝብም ተቀብሎ የስልጣን ባለቤት ለመሆን ፣ የሚጠቅመውን የመምረጥ የማይጠቅመውን የመሻር እና በሃገሩ ባይተዋር የማይሆንበት ስረዓት እንዲኖረው ወደ ትግሉ በቆራጥነት መቀላቀል ሃገራዊ ግዴታው ነው ።

No comments:

Post a Comment