ማለባበስ ይቅር ፣ ማሰመሰልም ይቅር፣
ወያኔን ለመጣል እንስራ በፍቅር፡፡
ዘረኝነት ይጥፋ ከመካካላችን፣
በኛ ተጨንቃለች ኢትዮጵያ ሀገራችን፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የተኩላዎች ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱ የሚታወቅ ነው ተኩላዎች ወደ ሕብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ወይም ሲገቡ በጣም ተወዳጅነት ያለው የሰው መልክ ይዘው ስለሚመጡ የምንቀርባቸውን ሰዎች በደንብ ማወቅ አለብን ራስን ለማሳወቅ የዘገየን ሰውን ለማወቅ የፈጠን እንሁን ካለማወቅ መሸወድ ይመጣል
Derartu Tulu
መሸውድ የዘላለም ጸጸት ያመጣል በተለይም በስደት ላይ የምንገኝ እህቶች እና ወንድሞች ይህንን በተግባር ማዋል ግድ ይሆንብናል፡፡ በቅርቡ የተከሰተ አንድ ነገር ልገልጽላችሁ እወዳለው ነገሩ እንዲህ ነበር መቼም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ፕሮፌሰር ይስሀቅ ኤፍሬምን የማያውቅ ይኖራል ብየ አልጠራጠርም ባለፈው በምርጫ 1997 ዘመን እኒህ ስመ ጥሩ አባት አንድ ያስታራቂ ቡድን በማማቋቋም መንግሰትን እና ተቃዋሚዎችን ለማደራደር ሞክረዋል ፡ ሙከራቸውም ለርሳቸው ግቡን መቶላቸዋል ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን ሊንጋለት የነበረውን ብርሀን ያጣበት ወቅት ነበር፡ ይህ ሰው የሰላምን ጎህ ካዳፈኑት አንዱ መሆናቸው መዘንጋት የለበትም፣ አሁንም አላፍር ብለው ተኩላዎቻቸውን ከሀገር ውጭ በመላክ በውጭ ሀገር የሚገኙ ተቃዋሚዎችን ለማዳከም በመስራት ላይ ይገኛሉ አሁን በቅርቡ ከኖርዌይ መንግስት ጋር በመደራደር ይህ ያስታራቂ ቡድን የሚሽን ስራውን ለመስራት ወደ ኖርዌይ ያመራው በታዋቂዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ በነበረቺው ደራርቱ ቱሉ ነበር፡ ደራርቱን ማንም ሰው የዚህ አይነት ወራዳ ስራ ትሰራለች ብሎ የሚጠረጥር ሰው የለም ለዚህም ነው መልካም ሰው መስለው ይገባሉ ብየ በመግቢያው ላይ የገለጽኩት በኦስሎ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ተውላጆች ደራርቱን እና አብረው የመጡትን ሰዎች ለምን ስራ እንደመጡ ስለነቁባቸው እና ለመደራደር የሚቀርቡትን ሰዎች በቁጥጥር ስር በማድርግ ስራውን እንዳይሰራ አስቁመዋቸዋል፡ የመጡበት ስራ ሳይሳካላቸው ተመልሰው እንዲሄዱ ምንም አይንት የመደራደሪያ ቀዳዳ እንዳያገኙ ያደረገውን የኦነግ አባላት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ክፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ፡፡ ይህ ነው ከኛ የሚፈለገው ደራርቱ ስኳር ልታልስ መምጣቷን ባለማወቅ ሁሉም ሰው ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ይሰጣት ነበር ደና ሰው ሲበላሽ ቅራሪ የለውም ይሉ የለ አበው.ሲተርቱ ዋ፡ደራርቱ. ዋ ኢትዮጵያ ማን ይሆን እውነተኛ ሰው ላንቺ የሚቆም?
በርቱ እንበርታ እንደዚህ ተባብረን ከሰራን የነጻነት ቀን ቅርብ ነው ከነጣቂ ተኩላዎች ጌታ ይጠብቀን፡፡
ወያኔ የሚሰራውን የአሰራር ስልት አበሻ የነደፈው ነው ቢባል ለእኔ ከእውነት የራቀ ነው ይህ የአውሮፓዊያን ቀመር ነው ፡፡ በደንብ ከተከታተላችሁት የሚያሰልሉን እርስ በርሳችን፣ ለጥቅም አደር ሆዳም የሚያገኙት ከመካከላችን ነው በዚህ አካሄድ ከቀጠሉ እርስ በርስ እንድንጋጭ የሚያደርግ ስልትም እንደሚፈጥሩ እርግጠኛ ነኝ እኛም በጣም መጠንቀቅ ያስፈልገናል ፡ ካለፈው የቅንጅት መበታተን ልንማር ይገባናል ቅንጅት እንደጅምሩ ቢቀጥል ኖሮ የወያኔ እድሜ እስከ አሁን አይቆይም ነበር በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣ ይባል የለ፡ ለቅንጅት መበታተን ዋና ምክንያት የሆነው ይህ አሁንም በስራላይ ያለው ያስታራቂ ቡድን መሆኑን መርሳት የለብንም ፡፡
በነግራችን ላይ ቅንጅት ይመራ የነበረው በጣም፡በሳል እና በሀገሪቱ አሉ በሚባሉት ምሁራን ነበር ከሀገርም አልፈው ለሌሎች ሀገሮች ነጻነት የሚከራከሩ ምህራኖችን ያካተተ ነበር እንደ ምሳሌ ዶክተር ያዕቆብን ብጠቅስ ለርዋንዳ ሕዝቦች መብት ሲከራከሩ የነበሩት የህግ ባለሞያ ናቸው ፡ወያኔ የሰራውን የመሰናክል ሩጫ ግን ማለፍ አልቻሉም ምክንያቱም የወያኔው የመብት ተሟጋች አስታራቂ በመምሰል መሀላቸው ገብተው እርስ በርስ በማጋጨት እንዲበተን አድርገውታል ወያኔም እድሜ ለፕሮፌሰር ይስሀቅ እያለ ብዝበዛውን እንደቀጠለ ይገኛል ለመሆኑ ፕሮፌሰር ይስሀቅ ማናቸው ? ሰማቸው እና ግብራቸው አብሮ የማይሄድ. ከማንኛው እንመድባቸው? ለወደፊት ማወቅ የሚገባን ነገር ቢኖር በሀገር ጉዳይ ላይ ሽምግልና እና የምልጃ ስራ የማይሰራ መሆኑን ነው ፡፡

ወያኔ ከሚጠቀምባቸው የተሻለ ስልት መጠቀም አለብን ያ ካልሆነ ግን ሰላም እንደናፈቀችን እኛም እናልፋለን ለመስራት በመጀመሪያ በውስጣችን ያሉትን እንደነ ደራርቱ እና ፕሮፊሰር ያሉትን ነጣቂ ተኩላዎች ለይቶ ማውጣት አለብን ፡፡ ወያኔ የተግባር አስፈሚ የሚጠቀምባቸው አንዳንድ ሆዳም ባለሀብቶችን መጠንቀቅ አለብን ፡እንደ ሼህ አላሙዲ ያሉ ሰዎችን ሀገር ወዳድ በማስመሰል ለሲምቦል ሲያቀርቡልን የቀረበው ማነው ብለን መጠየቅ አለብን እንዲህ አይነት ሰዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊወክሉ የማይችሉ ናቸው ሀገር በተበጠበጥች ቁጥር የግል ባለሀብቶች ቢዝነሳቸውን እንደፈለጉት ራን ማድረግ ይችላሉ ምክንያቱም የሰው ሀይልም ሆነ የገበያ ሁኔታ በርካሽ የማግኘት ቻንስ እንዳላቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ የሚሰሩትም ከገዡ አካል ጋር ተለጥፈው ነው ሀብቱ ቢሆን በነሱ ስም የተመዘበር የሀገሪቱ ገንዘብ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡ ባሳለፍናቸው 21 ዓመታት ሼህ አላሙዲ ከየት ወደየት እንደደረሱ ማየት ይቻላል ፡ በሀገር ውስጥ የሰላም መጥፋት ያለምንም ተወዳዳሪ ከሌቦች ጋር በመሻረክ የሀገሪቱን የገበያ ሁኔታ በቁጥጥር ስር አድርገውት ይታያል.፡ እንደዚ አይነት ሰው በጭራሽ ሀገር ሊወክል አይችልም ፡፡
እንደ መነሻ የፕሮፌሰር ይስሀቅን ሥራ ጠቀስኩ እንጂ ብዙ አይነት የማዳከሚያ ስልቶችን በተለያዩ ሰዎች እየተጠቀሙ ይገኛሉ ከጥንቱም ሰዎቹ በዚህ የማሰለል ስራ ልምድ ያላቸው ናቸው ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ታሪክ ልመልሳችሁ.. ደጃች ውቤ ናቸው ? የሰሩትን ስራ ታውቃላችሁ ?
የትግራይ ገዥ የነበሩት ደጃች ውቤ ስልጣናቸውን ለማስፋፋት ሲሉ የአማራውን ክፍለሀገር ለማጥፋትና በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ የአማራ ክፍለሀገር ገዥ የነበሩትን እራስ አሊን በአቡነ ሰላማ በማሰለል (በማስወገዝ ) የማዳከም ስራ የተጠቀሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አቡነ ሰላማ የአማራውን ገዥ የሆኑትን ራስ አሊን በገሀድ በማውገዝ ቀጥለው እንዳለ ደጃች ውቤ በበኩላቸው ግዙፍ ሰራዊታቸውን በመምራት ወደ በጌምድር አቀኑ በወቅቱ በጌምድር የንጉስ ግዛት ብትሆንም ሙሉ ስልጣን የነበራቸው ራስ አሊ ነበሩ፡፡ የነዚህ ወራሪዎች ቅድመ አባት የሆኑት ተንኮል የተሴረባቸው ደጃች ውቤ ንጉስ ዮሐንስ3ኛ እና ደጃች ጎሹን በማስተባበር በበላይ አዛዥነት የካቲት 9 1842 ዓ.ም በአማራው ሕዝብ ላይ የከፋ ጦር እንዳካሄደ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ሙከራውን ሞከሩ እንጂ ደጃች ውቤ አልተሳካላቸውም በራስ አሊ ቁጥጥር ስር ነው የወደቁት፡ ከታሪክ እንደምንረዳው በሰሜን በኩል ከጥንትም ጀምሮ ሰላም የለም በሌላ በኩል የትግራይ ክፍለሀገር ሁኔታውን ስንመለከት ደም አፍሳሽ፡ በሆነው የመሳፍንት ዘመን፡ የጎላ ሚና ነበረው ለማለት እንችላለን እርግጥ ነው የሸዋ ክፍለ ሀገር በራስ ገዥነት፡ለበርካታ ዘመናት ለመኖር እንደቻለ ይታወሳል ፡፡
የትግራይ ክፍለሀገር ገዦች ከጎንደር፡አቻዎቻቸው ጋር በነበራቸው ትስስር አንድ ጊዜ በመካከላቸው ሰላምና መረጋጋትን ሲያሳልፉ በሌላ ጊዜ ደግሞ አንዱ በሌላው ላይ በመዝመት ሲዋጉ አካባቢያቸውንም የጦርነት ቀጠና በማድረግ ይታወቁ ነበር ፡፡
በአሁኑ ወቅት እኔ እንደሚመስለኝ በደጃች ወልደ ስላሴ ከ1784 እስከ 1816 ዓ.ም የደረሰባቸውን የጦርነት በቀል እየተበቀሉን ያሉ ይመስለኛል፡፡ ነገሩ እንዲህ ከሆነ እኛም የደጃች ጉግሳነን ብለን እንነሳ፡ደጃች ጉግሳ የትግራይን መሪ ግብ ካስያዙት የመጀመሪያው ጀግና ተዋጊ ናቸው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ከውስጣችን አንድ ደጃች ጉግሳን መፍጠር ወይም ሆኖ መገኘት ነው ፡፡
እነሱ የስለላን ስራ ከደጃች ውቤ ውሸትና ክህደትን ከደጃች ወልደሥላሴ ይዘው የመጡ መሆኑን ማወቅ አለብን ዘር ከልጓም ይጠቅሳል ይሉ የለ አበው ሲተርቱ ፡፡ ለአንድ ወያኔ መዋሸትና ዋሾ መባል የማዕረግ ስም መሆኑን ልንረዳው ይገባናል ፡ የደጃች ወልደስላሴ ክህደት እንዲህ ነበር የትግራይ ገዥ ደጃች ወልደስላሴ የኢትዮጵያ ገዥ፡እራሳቸው እንደሆኑ በማስመሰል ከውጭ መንግስታት ጋር ግንኙነት ማድረጋቸው ነበር ፡ በመሆኑም ከእንግሊዝ መንግስት ጋር የፖለቲካና የንግድ ትብብር ውል መፈራረማቸው ይታወቃል ፡፡
ደጃች ወልደስላሴ ያወረሱአቸው የሸፍጠኝነት ውርስ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ወያኔ እንደ ጥሩ ተግባር ሲያስፋፉት ይታያል በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሰለሞናዊ ሥርወ መንግስት እስከ አለንበት ዘመን የተለያዩ የጭቆናና አፈና አገዛዞች ሲካሄዱ የቆየ መሆኑ ባይካድም የወያኔን ስርዓት ከሌሎቹ የተለየ የሚያደርገው፣ .
ደጃች ወልደስላሴ ያወረሱአቸው የሸፍጠኝነት ውርስ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ወያኔ እንደ ጥሩ ተግባር ሲያስፋፉት ይታያል በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሰለሞናዊ ሥርወ መንግስት እስከ አለንበት ዘመን የተለያዩ የጭቆናና አፈና አገዛዞች ሲካሄዱ የቆየ መሆኑ ባይካድም የወያኔን ስርዓት ከሌሎቹ የተለየ የሚያደርገው፣ .
1 . በዘር ላይ የተመሰረተ መሆኑ ፣
2 . አምባገነናዊ እና ጭካኔ የተሞላበት የሰው ልጆች የመናገርም ሆነ የመጠየቅ መብት የተነፈጉበት ስርዓት መሆንኑ ሌሎችም
በጣም ፡ የሚገርመው ከአንዳንድ ከድሮ የድርጅቱ ሰዎች የምንሰማው ነገር ነው የወያኔ መንግስት ከመጀመርያው ሲመሰረት ዋና አላማው ኢትዮጵያ የሚለውን ስም እና አማራን ማጥፋት ነበር ሲሉ አቶ ገብረመድህን አርአያ ገልጸዋል አቶ መለስ ዜናዊም 1974ዓ.ም አማራን ማጥፋት ቀላል ነው ማጥፋት አለብን ሲሉ በሙሉ ቃል ተናግረዋል ከጫካ እያለ ጥፋትን የተመኘልን ሰው ምኞቱ ተሳክቶለት እስከ እለተ ሞቱ የአማራን ልጆች እንደ እባብ ጨፍጭፎ፡የጨረሰ ሰው ነው ጌታ በቃህ ብሎ እርሱን ባያነሳው ፡ የማጥፋቱን ስራ አሁንም ተተኪዎቹ ተያይዘውት ይገኛሉ ይባስ ብለው በዓለም ታሪክ በጭካኔው በሚታወቀው በ2ኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ ያልተሰራውን ስራ ሲፈጽሙ ይታያሉ የወንድን ልጅ ብልት በገመድ በማሰር ለባለቤቱ አስይዞ ማስጎተት የሞት ሞት ይህ ነው ከዚህ በላይ ምንያድርጉ ሰው ከነነፍሱ መቅበር ነው የቀራቸው ወያኔ ለመቶ ዓመት የመግዛት ዓላማ ያለው የመምራት ችሎታ የሌለው፣ በመደራደር ከስልጣን የማይለቅ፣ የስስት ባህሪ ያለው፣ ከሟጨጨ የማይለቅ ዳሞትራ፣ የሰው ደም የመጠጠ መዥገር ልቡ የማይገኝ፡የእባብ ተምሳሌት በውሸት ላይ የተመሰረተ የሌቦች ጥርቅም ካለጦርነት አይለቅም ልንዋጋው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል አቶ ገብረመድህን አርአያ እስኪ ሁላችንም የአቶ ገብረመድህንን ያህል አስተዋፅኦ እናድርግ ልንዋጋቸው ይገባናል ካልተዋጋናቸው

ግን ፈራንም አልፈራንም፣ ብንወድም፣ ባንወድም ፣ቢዋጥልንም ባይዋጥልንም ደስ ቢለንም ብናዝንም ለሆዳሞች የተመቻቸ የአገዛዝ ስልት አስፈጻሚ መሆናችን መዘንጋት የለበትም በመተባበር ሁላችንም መጠቀም ያለብን ሰዓቱ አሁን ነው የሰው ዘር ጨርሶ ከኢትዮጵያ መሬት ሳይጠፋ ወገኔ እንነሳ ከግብጽና ከቱኒዝ ሕዝቦች ያየነውን እኛም በተግባር ላይ እናውለው ዘረኛው የወያኔ መንግስት በመደራደር ወይም በሰላም የሚለቅ እንዳልሆነ እያወቅነው እስከመቼ ድረስ ታፍነን እንኖራልን ለራሳችን ነጻነት መታገል ያለብን እኛው እራሳችን እንጂ ሌሎች ሀይሎች ሰላምን ሊያመጡልን የማይችሉ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ፡፡
ከመለስ ሞት ባሻገር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ እየታመሰች ትገኛለች የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሞት ለኢትዮጵያኖች ምንም ለውጥ አላሳየም ሕዝቡም ለማየት ሲጠባበቀው የነበረው ሰላም የውሀ ሽታ ሆኖ ነው የቀረበት፡ ፡ ሕዝብ ጦጣ ፈርቼ ዛፍ ብወጣ ነብር ቆየኝ የሚለው ዘይቤአዊ አባባል ነው የሆነበት ምክንያቱም የ3ሚኒስትሮች ከመጀመሪያው አያያዛቸው ሲታይ ሕዝቦች ሀገር ለቀው ተሰደዋል ብዙ ሰዎችም ከስራቸው ተፈናቅለዋል በፐርሰንት ስናየው ከባለፉት ዓመታት የግማሽ ዓመት ተጠቂዎችን ቁጥር የሚሸፍን ነው በሩብ ዓመት ውስጥ የግማሽ ዓመት ካሳየ ኢትዮጵያ የቀጣዩ እጣ ፈንታዋ ምንይሆን ?
ይህ ችገር እንዳለ ሆኖ የሚገርመው በአሁኑ ወቅት ሕዝቦቿን መግባ ማደር ያልቻለችው ሀገራችን ለኒውክለር ተጠቃሚ ለመሆን በስልጣኔ ከታውቁ ሀገሮች ጋር ለመፈራረም
መደራደሯ ነው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት ይሏል ይህ ነው፡ ለመሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያን ሕዝቦች የኑሮ ሁኔታ በሚገባ ያውቁ ይሆን ፟
ብሎ መገመት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በዓለም ላይ ካሉ ድሀ ከሚባሉ ሀገሮች ውስጥ አንዷ መሆኗን እያወቁ በዓለም ላይ ከታወቁ የማዕድን አምራች ሀገሮች ጋር ሲደራደሩ ትንሽ እፍረት አይሰማቸውም፡በመጀመሪያ፡የሕዝቦች ነጻነት ይከበር የኒውክለር ምርት ማምረቱ ቀርቶ፡፡ በጉዲፈቻ መልክ በመሸጥ ላይ ያሉት የህጻናት መብት ይከበር. በአሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ ልጆችን በጉዲፈቻ በመላክ የላቀ ስም አግኝታለች ልጆቹም ላሳዳጊ የሚሰጡት (የሚሸጡት )ከወላጆቻቸው ተሰርቀው መሆኑን አሁን በቅርብ በዴንማርክ ሀገር የተከሰተውን ጥሩ መረጃ መጥቀስ ይቻላል ለአቶ ኅይለማርያም ደሳለኝ ኒውክለር ከማምረት በፊት ለዜጎች ቅድሚያ ይስጡ፡ስል ሃሳቤን እቋጫለው፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ አያና ከበደ ከኖርዌይ
ጸሃፊውን ማግኘት ከፈለጉ ayanakebede@hotmail.com
No comments:
Post a Comment