FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 28, 2012

መንግስት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ


ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡

/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊውዘመንመጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ስራ አለመሆኑን፤ ነገር ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋልሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር
ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ ኃይሎች አሉያሉት /ጄኔራሉይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

/ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለውየኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነውብለዋል፡፡

ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነውየሚሉት /ጄኔራል ተክለብርሃንሕገመንግስቱንም ሆነ የሕዝቡን ሰላም የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባምብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ
ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡


No comments:

Post a Comment