FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, December 25, 2012

ከቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባዔ ምርጫ አዳዲስ አመራሮች አይጠበቁም ተባለ


ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ ጉባዔ በየካቲት ወር በመቀሌ ከተማ የግንባሩን አመራር ይመርጣል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም ምርጫው ግን ብዙም አዳዲሰ ለውጦች እንደማይኖሩት ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገለጡ

በግንባሩ ሕገደንብ መሰረት ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ የሚካሄደው ይኸው ጉባዔ በየካቲት ወር 2005 ሲካሄድ ግንባሩን ለቀጣይ ሁለት ዓመት የሚያገለግሉ አመራሮችን ይመርጣል፡፡

በዚሁ መሰረት የግንባሩ አባል ድርጅቶች እስከቀጣዩ ወር የራሳቸውን ጉባዔ በማካሄድ ለኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚነት የሚያገለግሉ እያንዳንዳቸው ዘጠኝ አባላትን የሚመርጡ ሲሆን እነዚህ በጠቅላላው 36 አባላት የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከመካከላቸው የግንባሩን ሊቀመንበር፣ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ በጉባዔው ላይ ያከናወናሉ፡፡

ይህ ጉባዔ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ በቅርቡ የተሾሙትን የግንባሩን ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ እና ምክትላቸውን አቶ ደመቀ መኮንን ያነሳል ተብሎ እንደማይገመት ታውቋል፡፡

በሕመም ምክንያት ረዥም የሕክምና ክትትል ላይ የሚገኙት የአህዴድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ በምክትላቸው አቶ ሙክታር ከድር ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አቶ አለማየሁ ቀደም ሲልም መልቀቂያ ከማቅረባቸው ጋር ተያይዞ በቅርቡ በተካሄደው የሶስት ምክትል /ሚኒስትሮች ሹመት ውስጥ ኦህዴድን መወከል የሚገባቸው እሳቸው የነበሩ ቢሆንም ምክትላቸው አቶ ሙክታር እንዲሾሙ ኦህዴድ በወከላቸው መሰረት አቶ ኃይለማርያም ካቢኔ ውስጥ መካተታቸው ይታወሳል፡፡
በተያያዘ ዜና በቅርቡ የተካሄደው ሹመት ብዙም ያላስደሰታቸው የህወሃት አባላት የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንዲዛወሩ ያደረጉት ከሁለት ዓመት በኃላ የጠ/ሚኒስትርነትን ቦታ እንዲይዙ ታቅዶ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶች አሉ።

የአቶ መለስ ሞት ከማንም በላይ ህወሃቶችን ያደናገጠና ሁኔታውንም ተከትሎ የተሰጡ ሹመቶች ነባር የሚባሉ ከፍተኛ የህወሃት አመራሮችን ጭምር እንዳላረካ የሚጠቅሱት የቅርብ ሰዎች፣  ትልቁ የህወሃቶች ስጋት ከእጃቸው የወጣውን ስልጣን መቼ መልሰው እንደሚያገኙት እርግጠኛ መሆን አለመቻላቸውና ብዙዎቹ አመራሮች ከፍተኛ ሃብት ከማፍራታቸው ጋር ተያይዞ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ነው ተብሎአል፡፡

ይህ ጉዳይ በህወሃቶች በሚስጢር ተመክሮበት አቶ ቴዎድሮስ ከጠ/ሚኒስትር ኃይለማርም ጋር   በቅርበት መስራት በሚያስችላቸው ቦታ በማስጠጋት 2007 . አገራዊ ምርጫን ተከትሎ በሚደረገው የጠ/ሚኒስትር ሹመት ብቁ ማድረግ የሚለው ዕቅዳቸው በፓርቲያቸው ተቀባይነት አግኝቶ መተግበሩን አስረድተዋል፡፡

እንደ ህወሃቶች ዕቅድ ከሆነ አቶ ኃይለማርያም ከሁለት ዓመት ስልጣን በኃላ መሰናበታቸው ግድ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጅ  ይህ የተባለው ዕቅድ መኖርና አለመኖሩን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም።

ኢህአዴግ ባስቀመጠው የመተካካት ዕቅድ መሰረት የብአዴን ጎምቱ የተባሉ አመራሮች በአዲስ መተካት ሚኖርባቸው ቢሆንም እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት እንደ እነአቶ በረከት ስምኦን የመሳሰሉ ነባር አመራሮች ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ስለመነሳታቸው ጉዳይ ምንም ዓይነት ፍንጭ አለመኖሩን ጠቁሟል።





No comments:

Post a Comment