FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, December 27, 2012

ለእርቅ ጉባኤ አሜሪካ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አባቶች በሽምግልና ኮሚቴ ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ አወጡ


ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር የሚገኙ አባታቶችን በሶስት ዙር ሲያደራድር የቆየውና ለአራተኛ ዙር ቀጠሮ ይዞ የተነሳው የሽምግልና ቡድን ባለፈው አርብ ያወጣው መግለጫ እንዳስቆጣቸው የገለጹት አባቶች ይቅርታ ካልተጠየቁ በተያዘው የእርቅ ንግግር እንደማይቀጥሉ አረጋግጠዋል::
በቤተክርስትያኒቱ መካከል እርቅ ለማውረድና ሰላምን ለማውረድ ሲንቀሳቀስ የቆየው አስታራቂ ቡድን አዲስ ፓትሪያርክ ለመምረጥ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወም ባለፈው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል::
ለእርቅ ንግግር ወደ አሜሪካ የተጓዙት ልኡካን ባልተመለሱበትና  ቀጣይ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ በያዙበት ወቅት በአንዳንድ አባቶች ግፊት እርምጃ ተገቢ አይደለም ሲል ነበር ሸምጋዩ ቡድን መግለጫ ያወጣው::
እንደ ሽምግልና ቡድኑ ሁሉ ፓትርያርክ ለመምረጥ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወምና እንደማይቀበሉ በማረጋገጥ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት መግለጫ የሰጡት አባቶች አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ሸምጋዮቹን በመውቀስ ያወጡት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኖል::
በሸምጋዩ ቡድን አርብ ታህሳስ 23/2005 መግለጫውን ሲያወጣ በአሜሪካ የነበሩትና ታህሳስ 15/2005 ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት አባቶች ከአዲስ አበባ ያወጡትን መግለጫ አሜሪካ በነበሩበት ቀን ታህሳስ 13/2005 እንደሆነ መደረጉ ግልጽ አልሆነም::
የልኡካን ቡድኑ አባላት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ገሪማ፡ ብጹእ አቡነ አትና ቲዎስ ፡ ብጹእ አቡነ ቀውስጦስ ፡ ንቡረ እድ ኤሊያስ አብርሀ ባወጡት መግለጫ ሸምጋዩ ቡድን ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍሯል በማለት ወቅሷል:: በሽምግልናውም ሂደት ወገንተኝነት ይንጸባረቅበት ነበር ሲሉ አክለዋል::
የሽምግልናው ኮሚቴ ይህንን ስህተቱን አምኖ ይቅርታ ካልጠየቀ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በሚደረግ ንግግር አንሳተፍም ብለዋል::
ለሰላም ያለን ፍላጎት ግን አይታጠፍም ሲሉም አጠቃለዋል::

No comments:

Post a Comment