FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 28, 2012

የቤተሰብ ምሽት በቶሮንቶ በደማቅ ሁኔት ተከበረ


ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በቶሮንቶ ከተማና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢሳት የቤተሰብ ምሽትን ቅዳሜ ዲሴምበር 22 ቀን 2012 ዓ.ም የዕለቱ ይክብር እንግዳ ታማኝ በየነ ከባለቤቱና ከቤተሰቡ ጋር እንዲሁም ከኦተዋ፣ ከተለያዩ የካናዳ ከተሞችና ከአሜሪካ የመጡ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።
በየዓመቱ የኢሳት የቤተሰብ ምሽትን ለማዘጋጀት ያቀደው የቶሮንቶ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የቤተሰብ ምሽቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ በጎና ጉልህ አስተዋጾ እያደረጉ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እውቅና የሚሰጥበትና በስራቸውም እንዲገፉበት የሚያበረታታበት ነው።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆነው ታማኝ በየነ ለሃገሩና ለወገኑ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የቤተሰቡንና የግል ህይወቱን መስዋዕት በማድረግ ፍትህና ርትዕ በጠፋባት ኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ የአገሩ ሉዓላዊነት እንዲከበር አምባገነኖችን በማጋለጥ፣ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለመብታቸውና ለአገራቸው ነጻነት ቆርጠው እንዲታገሉ በመቀስቀስና በማስተማር እየተጫወተ ላለው ጉልህ ሚና ማበረታታት የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን የበአሉ አዘጋጆች አስታውቀዋል።
በዚህ የቤተሰብ ምሽት ታማኝን ያሳደጉት ቤተሰቡና ህብረተሰብ እሱን በመቅረጽ ትልቅ ሚና ያላቸው መሆኑን ያብራራው የበአሉ ዝግጅት ኮሚቴ የታማኝ ቤተሰብ በተለይም ባለቤቱ ፋንትሽ በቀለና ሶስቱ ልጆቻቸው እየከፈሉ ያለው መስዋዕት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ታማኝን በአሁኑ ማንነቱ እንዲገፋበት ለሚያደርጉት ጥረት አርዓያ ቤተሰብ በመሆናቸው የበአሉ የመጀመርያ የክብር እንግዶች ሆነዋል ብሏል።
ለኢሳት ቤተሰብ ምሽት በቀጥታ በስልክ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የታማኝ እናት ልጃቸው ከድሮውም በራሱና በሌሎች ላይ ጥቃት ሲደርስ የማይወድ መሆኑን አስረድተው ለዚህ ጥሩ ተግባሩ እውቅና የሰጡትንና የሚደግፉትን ከልብ አመስግነዋል።
የበአሉ ዝግጅት ኮሚቴና ወጣቶቹ ለሱና ለቤተሰቡ ያበረከቱትን ስጦታ ከተረከበ በሁዋላ ታማኝ ባደረገው ቀስቃሽ ንግግር የተደረገለትን ከበሬታና ስጦታ አመስግኖ እሱ እንደዜጋ ለአገሩ ያደረገው አስተዋጾ ከሌሎቹ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት መሆኑን በማስረዳት “ብዙዎቹ ምንም ያላገኙባት ኢትዮጵያን ለአንድነቷ በገበያ ላይ በገመድ ተሰቅለዋል፣ ለባንዲራዋ በፈንጅ ላይ ተረማምደዋል፣ ለሉዐላዊነቷ ባምባገነኖች ተረሽነዋል። እኔ ያደግሁት ይህን እየሰማሁና እያየሁ በመሆኑ የማውቀውን እውነት በመናገሬ አክብራችሁኛል። ህይወትንም የሚጠይቅ መስዋዕት ቢመጣ በጸጋ እቀበላለሁ” ሲል አረጋግጧል።
በበአሉ የልጅ አለማየሁ ቴዎድሮስ፣ የአሉላ አባነጋና የአቡነ ጴጥሮስ ምስሎች በጨረታ ቀርበው ገቢ አስገኝተዋል።

No comments:

Post a Comment