FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, December 25, 2012

አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት በሁሉም የመንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ዘንድ በግዳጅ እየተሸጠ ነው


ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የስራ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት በሁሉም የመንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ዘንድ በግዳጅ በ 100 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተገለጸ::
ከሀገር ቤት የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በጠ/ሚሩ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት ከ 2000 ብር በላይ ደሞዝተኛ የሆነ በአንድ ክፍያ 100 ብር ለመግዛት ይገደዳል ከ2000 ብር በታች ደመወዝ ያለው እንደደሞዙ ልክ በየወሩ ይቆረጥበታል::
የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በስብሰባ ተነግሯቸውና ሳያቁ እንዲፈርሙ ተደርጎ ከደመወዛቸው ለአዲስ ራዕይ መጽሄት 100 ብር መወሰዱን ቢቃወሙም ሰሚ እንዳላገኙ አስታውቀዋል::
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በህይወት ዘመናቸው የሰሩትን ስራ አጉልቶና አኩርቶ ይተርካል በተባለው መጽሄት የግዢ  ድርድር የሚባል ነገር የለም ሁሉም ሰራተኛ በአንድ መቶ ብር የመግዛት ግዴታ እንዳለበት በግልጽ ተነግሯል እንደ ምንጮቻችን ዘገባ::

No comments:

Post a Comment