FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, December 31, 2012

ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ከ 18 አመት በታች ያሉ ታዳጊዎች ቁርዐን ትምህርት እንዳይሰጥ አዘዙ


ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናቶች የዲንና የአረብኛ ትምህርት እንዳይሰጣቸው የሚል ሃሳብ ማንሳታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮባቸዋል፡፡
መጅሊስ በፍትህ ሬዲዮ ለተለቀቀው ዜና የማስተባባያ መግልጫ በኢቲቪ ሊያወጣ ነው፡፡
ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ከ 18 አመት በታች ያሉ ታዳጊዎች ቁርዐንና የዲን ትምህርት እንዳይሰጥ የተናገሩትን ተከትሎ በፍትህ ሬዲዮ መዘገቧ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በአወሊያ ኮሌጅ ከዚህ በፊት ይሰጡ የነበሩት የአረበኛና የዲን ትምህርት እንዲቆሙ መደረጉንም እንዲሁ መዘገባችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም እነኚህ እውነቶች ለህዝብ ከተጋለጡ በኋላ መንግስትና የመንግስት ሹመኞቹ የመጅሊስ አመራሮች ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በመንግስት ትእዛዝ መጅሊሱ የአወሊያ ትምህርት ቤት ለሃይልስኩል ተማሪዎች ብቻ የአረብኛ ትምህርት እንዲሰጥ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ትናትና የአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር የአረብኛ መምህራንን አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት “መንግስት የአረብኛ ትምህርት እንዲሰጥ ፈቅዷል፣ ከዚህ በኋላ እናንተ መምህራኖች ትምህርቱን ለመስጠት በደንብ መዘጋጀት አለባችሁ ፡፡ ተማሪዎችን በአረብኛ ትምህርት ዘርፍና በመልካም ባህሪ የማብቃት ትልቅ ሃላፊነት ይጠብቃችኋል፡፡ ኦቨርታይም ጭምር በመስራት ይህን ማሳካት አለባችሁ” የሚል መመሪያ በስብሰባው ወቅት ለመምህራኖቹ ተላልፏል፡፡ ታዛቢዎች እንደሚሉት ግን የዲንና የአረብኛ ትምህርቱ በአወሊያ ኮሌጅ እንዳይሰጥ ተከልክሎና ተማሪዎቹ ተበትነው እያለ ፣ዜናዎችን ለማስተባበል ሲባል ብቻ የዲኑ ትምህርት ቆሞና የአረብኛ ትምህርት ተለይቶ በአወሊያ ሀይስኩል እንዲሰጥ መታዘዙ ተቀባይነት እንደሌለው እየተናገሩ ነው፡፡ እንደውም ይህ ሁሉ የሚያመለክተው መጅሊሱ በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ እንደሚሰራ አመላካች ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡
በ…ሌላ በኩልም ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናቶች የዲንና የአረብኛ ትምህርት እንዳይሰጣቸው የሚል ሃሳብ ማንሳታቸውን ተከትሎ በፍትህ ሬዲዮ ሳምንታዊ ዜና እወጃ ላይ ከተነገረ በኋላ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባ የመጅሊስ ፕሬዚደንት ከሳምንት በፊት በአንድ ስብሰባ ላይ “ዶክተር ሽፈራው እንደቀልድ አክራሪነትን ለመቀነስ በስብሰባ ላይ ከ18 አመት በታች ያሉትን ህፃናቶች የዲንና አረብኛ ትምህርት እንዳይሰጥ ይደረግ ይሆን? ብለው እንደቀልድ የተናገሩትን ጠቅላላ የስብሰባውን ሪፖርት ወስደው ለፍትህ ሬዲዮ ሰጡት ” በማለት በብስጭት ሲናገሩም እንደነበር ምንጮች አጋልጠዋል፡፡ አሁን ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ በመንግስትና በህገወጡ መጅሊስ መካከል ምክክር ከተደረገ በኋላ ከ18 አመት በታች ያሉ ህፃናቶች የቁርዐንና የዲን ትምህርት እንዳይማሩ ሊከለከል ነው እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሃሰት ነው ብሎ መጅሊሱ መግለጫ እንዲሰጥ ታዟል፡፡ በዚህ መሰረት መንግስት ትላንት ማክሰኞ 16 -4-2005 የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዝን ጋዜጠኞችን ወደ ህገወጦቹ መጅሊስ ቢሮ ልኮላቸው ኢንተርቪው ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡ ህዝቡም ይህን ቀድሞ ተረድቶ እንደከዚህ ቀደሙ የመንግስትንና የመጅሊሱን ግዜያዊ ተራ ፕሮፖጋንዳ ቀድሞ እንዲያውቅና ለመግለጫውም ቦታ እንዳይሰጠውና ተቀባይነት እንደማይኖረውም ከወዲሁ እንዲያውቁት ማድረግ አለብን ፡፡ፍትህ ሪዲዮም በዚህ አጋጣሚ የምታስተላልፈው መልዕክት፤ የመንግስት ባለስልጣናት በየስብሰባው አዳራሽ አፋቸውን ያለገደብ እየከፈቱ ህዝብን የበለጠ ከማስቆጣት እና ማስተባበያ ለማውጣት ከመንደፋደፍ ይልቅ መፍትሄው የህዝበ ሙስሊሙን መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው ትላለች፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
source: http://minilik-salsawi.blogspot.no/

No comments:

Post a Comment