FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 28, 2012

በአዲስአበባ አቶ መለስን የሚያወድሱ ፖስተሮች እየተነሱ ነው


ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- “ራዕይህን እናሳካለን”፣“አባይን የደፈረ መሪ”፣“ቃልህን እንጠብቃለን” እና የመሳሰሉ የውዳሴ ቃላት ጋር የአቶ
መለስን ምስል የያዙና በውድ ዋጋ የተሰሩ ፖስተሮች አዲስአበባ ከተማን ጨምሮ ክልሎችን ከማጥለቅለቃቸው ጋር
ተያይዞ ግንባሩ ባልተለመደ ሁኔታ ግለሰብ ወደማምለክ ደረጃ ማሽቆልቆሉ በራሱ አባላት ጭምር ከፍተኛ ትችትን
አስከትሎበታል፡፡
ሰሞኑን በአዲስአበባ በተለይ ከኡራኤል ቤ/ክ እስከ ፍትህ ሚኒስቴር የመኪና መንገድ አካፋይ መሃል ላይ በግምት
በ30 ሜትር ልዩነት ተደርድረው የነበሩ የአቶ መለስ ፖስተሮች እንዲነሱ ተደርጓል፡፡
ስለጉዳዩ አስተያየት የተጠየቀ አንድ የአዲስአበባ ነዋሪ ኢህአዴግ በተለይ አቶ መለስ ራዕይ በሚባለው ጉዳይ እጅግ
ተጃጅሎ ከርሟል፡፡
ስንትናስንት ችግር ባለበት ደሃ አገር በሚሊየን የሚቆጠር ብር ለመፈክር መጻፊያ ፖስተር የመንግስትና
የሕዝብ ገንዘብ ሲባክን መክረሙ እጅግ የሚያሰዝንና የሚያሳፍር ነው ብሏል፡፡
የፖስተሮቹ መነሳት፣አለመነሳት ለእኔ ትርጉም የለውም የሚለው አስተያየት ሰጪው የግንባሩ ካድሬዎች ቀድሞውንም መፈክር በመጻፍ ሥራ የተጠመዱት የሕዝብ ድጋፍ ያገኙ መስሎአቸው የነበረ ሲሆን ሕዝቡ ግን በአድራጎታቸው ማፈሩን ሲረዱ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጡበትን ምስል በሚያዋርድ መልኩ እየነቀሉ ለመጣል አላመነቱም ሲል ትዝብቱን ገልጾአል፡፡
የቀድሞ የህወሃት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ ሰሞኑን በአዲስአበባ ለታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ “የመለስ
ራዕይ” የሚለውን አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ በሚያጣጥል መልኩ “በግለሰብ ላይ የተቀመጠ ራዕይ ሳይሆን የሁላችንም እሴት
የሆነ የጋራ ራዕይ ነው ያለን” ሲሉ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል

No comments:

Post a Comment