ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባዎቹ ተደራዳሪ አባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የተካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሎስአንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት አባቶች አንደኛው የሆኑት ብጹነ አቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር አሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉአል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ አለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል::
ከርሳቸው ጋር አብረው የተጎዙት ሌላው የሽምግልና ቡድን አባል ዲያቆን አንዱአለም ዳግማዊ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም ፡ ሊቀካህን ሀ/ስላሴ ከእስር ተርፈው የተባረሩት የአሜሪካ ዜጋ በመሆናቸው እንደሆነም ተመልክቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከአዲስ አበባ ተወክለው በድርድሩ ተሳታፊ የነበሩት አባቶች ታህሳስ 13/2005 በአስታራቂ ኮሚቴው ላይ ያወጡትን መግለጫ ተገደው መፈረማቸውን ደጀሰላም ዘግቧል:: አባቶቹ ኤምባሲ መጠራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል::
ከደጀሰላም ዘገባ መረዳት እንደተቻለው አባቶቹ የተጠሩት አስታራቂውን ቡድን በሚያወግዘው መግለጫ ላይ ፊርማቸውን እንዲያሳርፉ ነው::
ይህንን በማቀነባበር አቢይ ሚና የተጫወቱት የልኡኩ ቡድን አባል ንቡረእድ ኤሊያስ አብርሀ መሆናቸውም በዘገባው ተመልክቷል::
በሌላም በኩል የሀገር ቤቱ ልኡክ አባል ብፁእ ዶ/ር አቡነ ገሪማ በደረሰባቸው የጤና ችግር በአሜሪካ ህክምና በመከታተል ላይ ናቸው::
አቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ምእመናን ለህክምና መዋጮ እያሰባሰቡ ይገኛሉ::
No comments:
Post a Comment