FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, December 25, 2012

አቶ በረከት ስምኦን ተጽእኗቸው እየቀነሰ የህወሃት ጡንቻ እየፈረጠመ መምጣቱ ተገለፀ


ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር መለሰ  ዜናዊ ማለፋቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረከ ውስጥ  ሚናቸው ጎልቶ የነበረው አቶ በረከት ስምኦን ተጽእኗቸው እየቀነሰ የህወሃት ጡንቻ እየፈረጠመ መምጣቱ ተገለጸ::
የአረና ትግራይ አመራር አባል የሆኑት አቶ አስራት አብርሃም የውስጥ ምንጮችን ጠቅሰው ባሰራጩት ጹሁፍ እንዳመለከቱት አቶ በረከት ስለ ኤርትራ የሰጡት መግለጫ  ህወሃትን አሰተባብሮባቸዋል::
አቶ በረከት ስምኦን የኤርትራ ተቃዋሚዎች ፓልቶክ መድረክ ላይ ባድሜ የኤርትራ ነው በማለት መናገራቸው  እና ኤርትራዊያን ከሃገር አንዲባረሩ ያደረጉት አቶ ስየ አብርሃም ናቸው ሲሉ መደመጣቸው የህወሃት ሰዎች በአቶ በረከት ላይ እንዲነሱ ምክንያት መሆኑም ተመልክቷል::
አቶ በረከት ኤርትራዊያን ከሃገር እንዳይባረሩ እርሳቸውና አቶ መለስ መሞከራቸውን ሆኖም አቶ ተወልደ ወ/ማርያም : አቶ ስየ አብርሃና  አቶ ገብሩ አስራት የማባረሩ ሂደት ዋነኞቹ ተዋናዮች መሆናቸውን መስክረዋል::
አቶ በረከት በዚህ ረገድ የሰጡት መግለጫ የህወሃትን ሰዎች በማስቆጣቱ ሚናቸው እየተገደበ ፡ተጽኑዋቸው እየቀነሰ መምጣቱን በዚህም የአቶ ሰብሃት ነጋ ቡድን እንዲያንሰራራ እድል መፍጠሩን ከጹሁፉ መረዳት ተችሏል::

No comments:

Post a Comment