ታህሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የተለያዩ የመንግስት አካላት ከፖሊስ ጋር በመተባባር በደሴ የሚገኙ መስጊዶችን ቁልፎች አዳዳስ ለተመረጡት የመጅሊስ አመራሮች እንዲያስረክቡ ማድረጋቸው ታውቋል።
በዛሬው እለት በከተማ የሚገኙ ዋና ዋና መስጊዶች ቁልፎች ለአዳዲሶቹ የመጅሊስ ተመራጮች እንዲረከቡዋቸው ተደርጓል።
በተመሳሳይ ዜናም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በሙስሊም መሪዎች ቤት ውስጥ ሆን ብሎ በማስቀመጥ ቪዲዮ እየተሰራ መሆኑንና ቪዲዮውም አመራሮችን ለመክሰስ እንደማስረጃ እንደሚቀርብ ታውቋል።
በመንግስት እና በሙስሊም ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ውዝግብ አንድ አመት ሊደፍን አንድ ወር እድሜ ብቻ ቢቀረውም መንግስት አብዛኛውን ሙስሊም የሚያስቆጣ እርምጃ ከመወሰድ ባሻገር ችግሩን ለመፍታት ሙከራ ሲያደርግ አይታይም።
No comments:
Post a Comment