FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, December 27, 2012

በደቡብ ክልል የዳውሮ ወረዳ ዞን ም/ቤት አባላት ዛሬ ከጠሩት ስብሰባ 1500 ሰራተኞች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገለጠ


ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች  ከዞኑ እንዳመለከቱት የክቢኒ አባላቱ የምረጡን ስብሰባ አድርገው በነበረ ጊዜ ህዝቡ የኔሰው ገብሬ የተሰዋበትን የሎሜ ከተማ ዋና ከተማ ዋካ ትሁን ጥያቄ ሳይመለስ ስለምርጫ  አናወራም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቷል::
የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በየኔ ሰው ገብሬና በህዝቡ ዘንድ ዋካ መሆን ይገባታል የሚል የነበረ ሲሆን የዞኑ የዴህዴን አመራር አባላት ዋካ መጤ ነዋሪ የመጣባት ከተማ በመሆኗ አይቻልም ሲሉ መቆየታቸው ተገልጧል::
ዛሬ በሎሜ ወረዳ የዞኑ የካቢኔ አባላት ሰራተኞችን ሰብስበው በቅርቡ በሚደረገው የወረዳ ምርጫ ደኢህዴን ኢህአዴግን ምረጡን ለመስበክ ሰራተኞችን ሰብስበው የነበረ ቢሆንም የዋካ ዋና ከተማነት ካልጸደቀ ከናንተ ጋር አንወያይም ሲል ነው 1500 ሰራተኛ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት::
ምንጮቻችን ከሎሜ ወረዳ ባደረሱን ዘገባ መሰረት የዞኑ የካቢኔ አባላት መከፋፈላቸውንም ለማወቅ ተችሏል::

No comments:

Post a Comment