FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, December 31, 2012

በአማራ ክልል 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀቁ / የአረና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በዶዘር ፈረሰ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀዋል። ፖሊሶች ስራቸውን መልቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በአንድ ስብሰባ ላይ አምነዋል።
ፖሊሶች ስራቸውን የለቀቁት በአስተዳደር ጫና እና ከስራቸው ጋር የማይጣጣም እና የኑሮ ውድነቱን ለማቋቋም የማያስችል ክፍያ ስለማይከፈላቸው መሆኑን ይገልጻሉ።
በክልሉ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት ፖሊሶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞችን እያስመረረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ለአባይ ግድብ ማሰሪያና ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ ማሳኪያ በሚል ሰራተኞች መዋጮ እንዲከፍሉ መገደዳቸው ኑሮአቸውን የከፋ እንዲሆን እንዳደረገው ሰራተኞች ይገልጻሉ።



የአረና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በዶዘር ፈረሰ 
ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሁመራ የሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት በዶዘር እንዲፈርስ ከተደረገ በሁዋላ የድርጅቱ ጽህፈት ቤትም ተዘርፎአል። በተመሳሳይ መንገድም የድርጅቱ አባል የሆኑት የአቶ ገብረእግዚ ናዩ ቤት ያለምንም ማስጠንቀቂያ እንዲፈርስ ተደርጓል።
በተንቤን የድርጅቱ አባል የሆኑት አቶ ጸጋየም መታሰራቸው ታውቋል። በአቶ ገብሩ አስራት በሚመራው አረና ፓርቲ ላይ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የሚወስዱት እርምጃ እየከፋ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment