FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, January 31, 2013

ለአባይ ግድብ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ የተሰበሰበው ከ35 በመቶ በታች ነው


ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ይፋ ከተደረገበት ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች እና ግለሰቦች ቃል ከተገባው 600 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 11 ቢሊዮን ብር ውስጥ እስካሁን ለመሰብሰብ የተቻለው ከ200 ሚሊዮን ዶላር ወይም 4 ቢሊዮን ብር ሊበልጥ አልቻለም።
መንግስት  ሰራተኞችን እንዲሁም የንግድ ድርጅቶችን በማስገደድ እስካሁን ያሰባሰበው ገንዘብ ፕሮጀክቱን ለማሰራት ከሚፈጀው ገንዘብ ጋር ሲተያይ እጅግ አነስተኛ ነው። በየጊዜው የሚጨምረው የእቃዎች ዋጋ ባለበት ቢቆም እንኳ ግድቡን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማስጨረስ የሚያስፈልገው  ከ90 ቢሊዮን ያላነሰ ገንዘብ ለመሰብሰብ እጅግ አዳጋች እንደሚሆን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ሲያስጠነቀቁ ቆይተዋል።
በፕሮጀክቱ ላይ በተለያዩ ሞያዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት በማኔጅመንቱና ስራውን በሚሰራው የጣሊያኑ ሳሊኒ የአስተዳደር ችግር ምክንያት ስራው በተፈለገው ፍጥነት እየሄደ አይደለም። ግንባታው በታቀደለት በአራት አመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደማይችል ሰራተኞች በእርግጠኝነት ይናገራሉ። መንግስት የግድቡ 14 በመቶ ተጠናቋል በማለት ቢያስታውቅም፣ በተያዘለት የጊዜ ገድብ ያልቃል የሚለውን በእርግጠኝነት ከመናገር ባለቀበት ጊዜ ይለቅ የሚል ቅስቀሳ ማካሄድ ጀምሯል።
መንግስት ህዝቡ ለግድቡ ያለው ስሜት መቀዛቀዙን እና መዋጮውም እያነሰ መምጣቱን በመመልከት አዳዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ለመዘርጋት አቅዷል።
ግድቡን ለመስራት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ይጠበቅ የነበረው በውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ቢሆንም፣ የኢህአዴግ ደጋፊ ከሆኑ የዲያስፖራው አባላት በስተቀር አብዛኛው ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆኑ ገዢውን ፓርቲ ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።
የአባይ ግድብ የአረቡ አብዮት በተነሳ ማግስት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል / በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ ራሱዋን መጸዳጃ ውስጥ በመግባት አጠፋች


ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ቀጠሮ ሰጥቷል።
የችሎቱ ዳኛ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እና አሳታሚው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ማስተዋል ብርሀኑ መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ ብይኑን ለመስጠት ለየካቲት አንድ ቀጠሮ ሰጥተዋል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች በችሎቱ ላይ አልተገኙም። በችሎቱ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የጋዜጠኛው ቤተሰቦች፣ አድናቂዎችና ስራ ባልደረቦች ተገኝተዋል።


በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ ራሱዋን መጸዳጃ ውስጥ በመግባት አጠፋች

ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ገነቴ ጌታቸው የተባለችው ተማሪ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ራሱዋን በመወርወር ያጠፋቸው ባለፈው ሳምንት ነው። በትምህርቷ ከፍተኛ ውጤት የነበራት ተማሪ ገነቴ ራሱን  ለማጥፋት ለምን እንደወሰነች በትክክል ለማወቅ ባይቻልም ተማሪዎች እንደሚሉት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው ተማሪዎች የውሀ፣ የመጸዳጃ እና ሌሎች አገልግሎቶች አልተሟሉልንም በሚል ተቃውሞ ከማስነሳታቸው ጋር ሊያያዝ  ይችላል። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸውን በማስቸገር በሚላክላቸው ገንዘብ የፕላስቲክ ውሀ  ሲገዙ መቆየታቸውን ያወሱት የሟቿ ባልደረቦች፣ ይሁን እንጅ ተማሪዋ የመጣችበት ቤተሰብ ይህን ለሟሟላት ባለመቻሉ ተማሪዋ በችግር ውስጥ ትገኝ ነበር ብለዋል። አሟሟቷንም ከገንዘብ ችግር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ትምህርታቸውን አቁመው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ግቢያቸው ተመልሰው መደበኛ ትምህርት የጀመሩ ቢሆንም፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግን አሁንም በዩኒቨርስቲው አካባቢ በብዛት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪዎችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Wednesday, January 30, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam Jan 30 2013 Ethiopia


የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ ወጣ


የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።
ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ።
“ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ የተጠቀሙበት ዋንኛ ስልት አባይ ጸሃዬን “ከውህዳኑ” ጋር በማሰለፍ ነበር። ዛሬ ለህወሃትና ለትግራይ ህዝብ በትግርኛ ቋንቋ ተጽፎ ተሰራጨ የተባለውና ይህንኑ መረጃ ዋቢ በማድረግ ኢየሩሳሌም አርአያ በተለያዩ ድረገጾች ይፋ እንዳደረጉት አቶ አባይ ጸሐዬ የተመደቡት ወጥመዱ ከተጠመደባቸው ዘንድ ነው።
“ድርጅትህ ኢህአዴግ እስከዛሬ ታግሎ እዚህ አድርሶሃል። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የሆነው ባለ ራዕዩን መሪህን በቅርቡ አጥተሃል” የሚል የአምልኮ መሪ ቃል ያለበት የጥሪ ወረቀት “ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ” በማለት ጥሪ አቅርቧል። ኢየሩሳሌም አርአያ ቃል በቃል በትምህርተ ጥቅስ አኑረው ባሰራጩት በዚህ ጉልህ ዜና “እነ አቶ በረከት፣ ወ/ሮ አዜብ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ” ወረቀቱን አዘጋጅተው እንዳሰራጩ ያስረዳል።
በኢየሩሳሌም አርአያ ዜና ላይ እንደተመለከተው እነ አቶ ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሐዬ፣ አለቃ ጸጋዬ ከነባለቤታቸው የትግራይን ህዝብ ለጠላት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ያወሳል። “… የኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ” የተጠቀሱትንና ሌሎች ደጋፊዎቻቸውን “ጅቦች” ሲል የሚጠራው መልዕክት፣ “… ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው” ሲል ያሳስባል። እነማን እንደሆኑ በግልጽ ሳይዘረዘር “የተወገዱ ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የህዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው” የሚል ማስጠንቀቂያ ያስቀምጣል። በስተመጨረሻ “ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል” ይላል።
“የኢህአዴግ ስኬት የመስመር እንጂ የግለሰብ አይደለም” በማለት የመለስን አምልኮ ለመቃወም ቀዳሚ የሆኑት አቶ ስብሃት ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ካስረከቡ በኋላ ከድርጅቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት የላላ መሆኑን ለማሳየት እንደ ሩቅ ተመልካች አስተያየት ሲሰጡ ባብዛኛው ባልተለመደ መልክ ይዛለፉ ነበር። በተለይም አቶ በረከትን የማኮሰስና ምናምንቴ አድርጎ የማሳየት ስልት ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ አለመግባባቱ ሊከሰት ግድ እንደሆነ አስቀድመው የተነበዩም ነበሩ።
“… መለስ ስለሌሉ የወንበር ቡቅሻው የማይቀር ነው። በድርጅቱ አመራሮች ዘንድ የሌባና ፖሊስ፣ የሃይል ሚዛንና ቅኝት፣ አሰላለፍን የማሳመር ሰልፍ እየታየ ነው፤ … የመለስ ማለፍ በድርጅቱ ውስጥ ታፍኖ የቆየውን ቁርሾ ማፈንዳቱ አይቀርም…” ሲሉ ኦክቶበር 25 ቀን 2012 ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ የሰጡት አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ የኢህአዴግ ሰው፣ የኢህአዴግ ድልድይ ተሰብሯል፤ የጋራ ነጥብም የለውም ብለው ነበር።
አውራምባ ታይምስ በበኩሉ ምንጩን አዲስ አበባ በማለት በተመሳሳይ የህወሃትን አደጋ ውስጥ መውደቅ ሲያበስር በስም ከዘረዘራቸው አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋን አልጠቀሰም። ኢየሩሳሌም አርአያ አቶ በረከት የሚዘውሩትና የእነ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወገን በዋናነት ለመምታት ያሰበው አቶ ስብሃት ነጋን እንደሆነ ለአባላት ተበተነ የተባለውን የማስጠንቀቂያ ወረቀት በመጥቀስ ይገልጻል።
አውራምባ ታይምስ “እያጣራሁ አቀርበዋለሁ” በማለት ያወጣው ትኩስ ዜና ለህወሃት አባላት ተሰራጨ የተባለውን ደብዳቤ “ማን እንደጻፈው አልታወቀም” በማለት ብዥታ የሚያጭር መልክት ሲያስተላልፍ፣ ኢየሩሳሌም አርአያ ከአውራምባ ድረገጽ ባለቤት አቶ ዳዊት ከበደ በተለየ መልኩ ዜናውን በትነው አስረድተዋል። በሁሉም በኩል እንደተጠቀሰው ህወሃት ቀውስ ውስጥ ተነክሯል።
በየካቲት ወር በሚደረግ ድርጅታዊ ግምገማ ጠራርገው እንደሚያስወግዷቸው እንደ ከባድ ሚዛን ቦክስ ቀጠሮ በመያዝ እነ አቶ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይና አለቃ ጸጋዬን በመጥቀስ የተሰራጨው ወረቀት በስተመጨረሻ ስብሃት ነጋ ላይ ክርኑን አስደቁሶ እንደሚያበቃ የህዋሃትን ጓዳ አስመልክቶ በተደጋጋሚ ለየት ያለ ዜና የሚያስነብቡት ኢየሩሳሌም አርአያ ያበቃሉ።
ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው የነበሩት የኢህአዴግ ሰው ይህንን ዜና አስመልክተው ምን አስተያየት እንዳላቸው ጠይቀናቸው ነበር። “በሌሎቹም አቻ ድርጅቶች ውስጥ በተመሳሳይ ይህ ሁኔታ ይከሰታል። የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። ለጊዜው ደኢህዴንና ብአዴን አንድ ላይ መሆናቸውን ያስታወቁት እኚሁ አስተያየት ሰጪ የኦህዴድ አቋም አለመጥራቱን ነው የሚናገሩት።
“የድጋፉ ጉዳይ የፎርሙላ ነው። ዶ/ር ደብረጽዮንና በረከት ስለላውን፣ ጦር ሃይሉን፣ የፖሊስና የልዩ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩት በአሸናፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለውም” ካሉ በኋላ አቶ ስብሃት ሰሞኑን “አማራውን ከሰደብኩ እኔ ታምሜያለሁ ማለት ነው ሆስፒታል መሔድ አለብኘኝ” በማለት የሰጡት መግለጫ ሲዘልፉትና ሲረግሙት የኖሩትን አማራና ብአዴንን ተለሳልሶ ለመቅረብ ያደረጉት እንደሆነ በተዋረድ ለብአዴን አባሎች መገለጹን እንደሚያውቁ አስረድተዋል።
“ምንም ተባለ ምን በመከላከያውና በደህንነቱ ሃይል ተጠቅመው የፈለጉትን መወሰንና የማስወሰን፣ ባላቸው በሚሰራው የፖለቲካ መዋቅር እስከታች መመሪያ በማውረድ የእነ በረከት ወገን ባለድል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ቀድሞ ታጋይ የነበሩ፣ የደህንነት ሃይሉን እየረዱ ብር የሚያመርቱ ግርግሩ ስለማይመቻቸው ሃይል ካለው ወገን ጋር በመሆናቸው እነ ስብሃትን ያቀላጥፏቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግለሂስ አድርገው አርፈው ለመቀመጥ ካልተስማሙ ብቻ ነው” በማለት አስተያየታቸውን ይደመድማሉ፡፡
ይህንን መረጃ በሚያጠናክር መልኩ ከዚህ በፊት ከጻፍናቸው ዜናዎች መካከል አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የመለስ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውንና አቶ መለስ ወደ ውጪ ሲወጡ የሥልጣኑን ቁልፍ የሚሰጡት ለአቶ በረከት እንደሆነ፤ የአቶ ሃይለማርያም ሹመት መነሻውም በዚሁ ቀደም ሲል በተፈጠረ “የቤተሰብ መሰል” ግንኙነት መሆኑን በመናገር ስማቸው ሳይጠቀስ ቃላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የሰጡ የኦህዴድ ሰው ጠቅሰን መጻፋችን የሚታወስ ነው፡፡ አቶ መለስ በሞቱ ማግስት ከኢህአዴግ ምክርቤት እና ከፓርላማው ውሳኔ በፊት አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚ/ር ሆነው እንደሚቀጥሉ በመናገር የተጠባባቂ ጠ/ሚ/ርነት ሥልጣን ይዘው እንደሚሠሩ አቶ በረከት በወቅቱ በሰጡት ቃለምልልስ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሃይለማርያም ለፎርማሊቲ በፓርላማ ፊት ቀርበው ምህላ እንደሚፈጽሙ አቶ በረከት በግላቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው ይህንኑ ቤተሰባዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን መዘገባችን የሚጠቀስ ነው፡፡

http://www.goolgule.com

የሙስሊም መሪዎች የችሎት ውሎ አስቂኝ ነው ተባለ


ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በዝግ ችሎት በሚካሄደው የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ 190 ምስክሮች እንደሚቀርቡ አቃቢ ህግ ቢያስታውቅም እስካሁን የቀረቡት ምስክሮች 11 ናቸው። ምስክሮችን የመስማት ሂደቱ በ10 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ በአሁኑ አካሄድ  አቃቢ ህግ የምስክሮችን ቁጥር ካልቀነሰ በስተቀር በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ላይጠናቀቅ ይችላል።
የውስጥ ምንጮች እንደገለጡት አቃቢ ህግ ምስክሮችን  ሲያቀርብ የአባታቸውን ስም ብቻ በመጠቀም ነው። ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጋ ምስክሮቹ የመኖሪያ አድራሻቸው ፣ ስራቸውና ማንነታቸው እንዲገለጥ ለዳኞቹ ቢያመለክቱም፣ ዳኞቹ “የምስክሮችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ምስክሮቹ አድራሻቸውንም ሆነ ስራቸውን እንዲገልጡ አይገደዱም” የሚል ምክንያት በመስጠት ጥያቄውን አልተቀበሉትም።
አቶ ተማም ”በህገመንግስቱ አንቀጽ 20 መሰረት አንድ ጉዳይ በዝግ ችሎት ሊታይ የሚገባው አገር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆን ብቻ ነው በማለት” ቢከራከሩም  ዳኞቹ ”የምስክሮች ደህንነትም የአገር ደህንነት ነው” በማለት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸውን ምንጫችን ገልጸዋል።
ጠበቃ ተማም ” በ1997 ዓም በቅንጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ሂደት ላይ  እንደተደረገው የተከሳሾች ቤተሰቦች እና ዘመዶች  ባይቀርቡ እንኳን ቢያንስ የውጭ እና የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የውጭ ዲፕሎማቶች እንዲገኙ ችሎቱ ፈቃድ ይስጥ በማለት ቢጠይቁም” ዳኞቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ክርክሩ ያለታዛቢ እንዲቀጥል ሆኗል።
ምስክሮቹ ተከሳሾች በአደባባይ የተናገሩትን ከመድገም ውጭ እስካሁን አንድም አዲስ ነገር አለመናገራቸው ታውቋል። ምስክሮቹ የተመሰከረባቸውን ተከሳሾች ጠቁሙ ሲባሉ ሌሎችን ሰዎች እንደሚጠቁሙ፣ እስረኞችም በምስክሮች ድርጊትና በፍርድ ቤቱ ሂደቱ ድራማ እየተዝናኑ መሆኑ ታውቋል።
አጠቃላይ የፍርድ ሂደቱ የተበላሸ እንደሆነ የተረዳው መንግስት፧ ከውርደት ለመዳን በሚል  የፍርድ ሂደቱን በዝግ ችሎት እንዲካሄድ ማድረጉን አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ህግ ባለሙያ ተናግረዋል።

በጉርዳፈርዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረጋጣ ቀጥሏል


ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ዞን በጉርዳፈርዳ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረገጣ መቀጠሉ ተገለጸ።
በወረዳው ባለፈው ታህሳስ አንዲት የ8 ልጆች እናት በጥይት ሲገደሉ፣ ሁለት ህጻናት በመስተዳድሩ መኪና ተገጭተው መሞታቸውን የመኢአድ ም/ሊ/መንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ለኢሳት ገልጸዋል።
ታህሳስ 28/ 2005 ከምሽቱ 4 ሰአት ሲሆን 5 መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች የ8 ልጆች እናት የሆኑትን ወ/ሮ አይቼሽ ስጦታውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደገደሉዋቸው ነው ም/ ሊቀመንበሩ የተናገሩት።
ጥር 15 ቀን 2005 ዓ/ም ደግሞ የ4 እና የ7 አመት ህጻናት በመስተዳድሩ መኪና ተገጭተው ህይወታቸው ማለፉን ከአቶ ወንድማገኝ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሎአል።
ሌሎች 23 የአማራ ተወላጆች በወህኒ ቤት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውንም የመኢአድ ተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበር አክለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማናገር ብንሞክርም አልተሳካልንም።

ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት የህትመት ዋጋ ጭማሪ አደረገ


ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-በማሽኖች እርጅናና በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ውስጥ የሚዋልለው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጦች የሕትመት ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፡፡

ማተሚያ ቤቱ በተለይ ባለቀለም ጋዜጦችን ተቀብሎ የማተም አቅሙ ከጊዜ ወደግዜ እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር
ተያይዞ ብዙ ጋዜጦችን በወቅቱ ማተም ባለመቻሉ በተለይ ቅዳሜ እና እሁድ የሚወጡ ጋዜጦች _ማለትም
ሪፖርተር፣ፎርቹን፣ካፒታል ጋዜጦች ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ መዳረጋቸው ተመልክቷል ፡፡

በደካማ አገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ የሚዳክረው ይኸው ማተሚያ ቤት ባለፈው ሳምንት በድንገት እስከ 12 በመቶ
የሚደርስ ጭማሪ በጋዜጦች የህትመት ዋጋ ላይ አድርጓል፡፡ ጭማሪው በተለይ ወትሮውም ከእጅ ወደአፍ ገቢ
ያላቸውን ጋዜጦች በፍጥነት ከገበያ ሊያስወጣ ይችላል የሚል ግምት አሳድሮአል፡፡

ማተሚያ ቤቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የዋጋ ጭማሪ ሲያደርግ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡ይህን ተከትሎም
እንደሪፖርተር ያሉ ጋዜጦች መሸጫ ዋጋ 10 ብር መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

ማተሚያ ቤቱ የህትመት ሥራ ውል ከጋዜጦች አሳታሚዎች ጋር ለመዋዋል ረቂቅ ሕግ አዘጋጅቶ በአሳታሚዎች
ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞት ሥራ ላይ እንዳይውል ከተደረገ ወዲህ እንደፍትህእናፍኖተ ነጻነትያሉ ጋዜጦችን
ከሕግና ከሥርዓት ውጪ አላትምም ከማለት ጀምሮ እያተማቸው ያሉ ጋዜጦችን ብዙውን ጊዜ በማሽን ብልሽት
በማሳበብ በሰዓቱ ወጥተው እንዳይሰራጩ እንቅፋት በመሆን ለኪሳራና ለአላስፈላጊ ወጪ በመዳረግ ላይ እንደሚገኝ
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ገልጸዋል፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የፕሬስ ነጻነት በተግባር እንዳይረጋገጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ከፍተኛ ጥረት
በሚያደርግበት በዚህ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ የሚታተሙ የፍቅርና የኪነጥበብ መጽሔቶች ሳይቀር ጭልጥ ብለው
የፖለቲካ ጉዳዮችን ከማስተናገድ አልፈው የሕትመት መውጫ ጊዜያቸው ከወር ወደ 15 እና ሳምንት ዝቅ እያደረጉ
መምጣት፣የነፍስ ወከፍ ኮፒያቸውም ከጋዜጦቹ በሚያስከነዳ መልኩ በአማካይ እስከ 30 መድረሱ ሌላ ራስምታት
እንደሆነበት ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡

ታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ባልደረቦቹ  የሚያዘጋጁት አዲስ ታይምስ መጽሄት ባለፈው ቅዳሜ ሳይወጣ
መቅረቱን መዘገባችን ይታወሳል።

የአቶ ጁነዲን ያለመከሰሰ መብት ያለመነሳት ጉዳይ ማነጋገሩን ቀጥሏል


ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት በአጀንዳ መልክ ለፓርላማ ቀርቦ
የነበረውና ባልታወቀ ምክንያት ፓርላማው እንዳይወያይበት በተደረገው የቀድሞ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ
አባልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ ሕግ አስፈጻሚው አካል አሁንም ዝምታን መምረጡ
አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል፡፡

ፓርላማው ከሁለት ሳምንት በፊት ባቀረበው አጀንዳ የአንድ የም/ቤት አባል ያለመከሰሰ መብት ስለማንሳት
በሚል ለውይይት አጀንዳ መያዙን ካስታወቀ በኃላ በድንገት ስብሰባው ከተጀመረ በሁዋላ ለሌላ ጊዜ
መተላለፉ በአፈጉባዔው በኩል ተገልጾአል፡፡

የፓርላማው ምንጮች እንደገለጹት አጀንዳው በፓርላማው ከኦሮሚያ ደራ ወረዳ ተመራጭ የሆኑትን አቶ
ጁነዲን ሳዶን የሚመለከት ነበር፡፡

ሆኖም ባልታወቀ ምክንያት አጀንዳው እንዲያድር ከተደረገ በኋላ ላለፉት አስራአምስት ቀናት
በላይ ዝምታ መመረጡ የብዙዎችን ትኩረት መሳቡ ታውቋል፡፡

አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤታቸው / ሐቢባ መሐመድ አዲስ አበባ ከሚገኘው ሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና የተለያዩ
መጽሐፍትን ተረክበው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ከተያዙበት ከሐምሌ 9 ቀን 2004 . ጀምሮ ከመንግስታዊ
ኃላፊነታቸው በተጨማሪ በመስከረም ወር መጨረሻ የዓመቱ መደበኛ ሥራውን የጀመረው ፓርላማ ተገኝተው
አያውቁም፡፡

ከባለቤታቸው ጥፋት ጋር ተያይዞ ከኦህዴድ አመራርነት ተገምግመው እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን
በጠ/ሚ ኃይለማርያም አዲሱ ካቢኔም ተወግደው በአቶ ሙክታር ከድር መተካታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባለቤታቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክሳቸውን እየተከታተሉ ቢሆንም ከሳዑዲ ኤምባሲ ጋር ከነበራቸው
ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሟች እናታቸውን ኑዛዜ ለማስፈጸም የገንዘብ ዕርዳታ የጠየቁት ራሳቸው መሆናቸውን
በመግለጽ ባለቤታቸው በጉዳዩ እጃቸው እንደሌለበት በይፋ ቢናገሩም እስካሁን የተጠየቁበት ሁኔታ አለመኖሩ
የህግ ሥርዓቱን ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል፡፡

ፓርላማው ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት ያደረገው ሙከራም የከሸፈበት ምክንያትም ለብዙዎች
እንቆቅልሽ እንደሆነ ነው፡፡ በተያያዘም ነሐሴ 14 ቀን 2004 . ባለቤታቸውን አቶ መለስ ዜናዊን
በድንገተኛ በሞት ያጡት / አዜብ መስፍን ከሐዘናቸው ካገገሙም በኋላ በፓርላማ ውስጥ ተገኝተው
እንደማያውቁ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ፓርላማው 3 ዓመት የስራ ዘመኑን በመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን መደበኛ ስብሰባዎችን
እያስተጓጎለም ቢሆን 15 መደበኛ ስብሰባዎችን ያካሄደ ቢሆንም የፓርላማው አባል የሆኑት / አዜብ
በአንዱም ስብሰባ ላይ አልታዩም፡፡

እንደ  ምንጮቻችን ገለፃ አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በቁም የተነሱትን ፎቶግራፍ ሁሉም
አባላት ሊያዩት በሚችሉበት ሁኔታ ፊት ለፊት የተሰቀለ ሲሆን ይህ ፎቶ በትልቁ ፊት ለፊት መሰቀሉ በብዙዎቹ
የፖርላማ  አባለት ዘንድ አሁንም ፖርላማውን እየመሩ ያሉት እርሳቸው እንደሆኑ የሚያሳስብ መንፈስ
ፈጥሮባቸዋል::


Tuesday, January 29, 2013

የኤርትራ ወጣቶች በሮም የሚገኘውን የኤርትራ ኢንባሲ ተቆጣጠሩት

They say that we are romantic revolutionaries. It is true we are so different, we are willing to give their lives for what we believe.

ESAT Daily News Amsterdam 29 January 2013 Ethiopia


አቶ ዱባለ ገበየሁና ሁለቱ ዐቃብያነ ህጎች ክስ ተመሰረተባቸው


ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን ተነስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ አቶ ዱባለ ገበየሁ ፣  አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ     ትናንት ከሰዓት በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ግለሰቦቹ  ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳትና በማሳመጽ ፣ ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር  እንዲሁም የመንግሥትን ንብረት በአመጽ በማስወደም ወንጀል ተከሰዋል።
ኢሳት ያለውን የመረጃ ሰንሰለት ተጠቅሞ አቶ ዱባለን በእስር ቤት ውስጥ አነጋግሮታል::
ከዳውሮ ዞን ፖለቲካ ክፍል በተገኘው ምስጢራዊ መረጃ መሠረት በታሰሩት በእነ አቶ ዱባለ ገበየሁና በሌሎችም ላይ የሐሰት ማስረጃ ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው። ገንዘብ እየተከፈላቸው ለመመስከር የተዘጋጁ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በዞኑ የሚታየው አለመረጋጋት ያሳሰበው መንግስት ግለሰቦቹ በአካባቢው የሚደረገውን ተቃውሞ በማደራጀት በኩል እጃቸው አለበት በሚል እንዳሰራቸው፣ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ድርጅት የደቡብ ክልል ዋና አደራጅ አቶ ዱባለ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።
አቶ ዱባለ በክልሉ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር እርሳቸው የኢህአዴግ አባል በነበሩበት ጊዜ በተለይም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እና  የደኢህዴግ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ አሰፋ ቤተሰቦቹን እያሾመ ነው በማለት ገምግመዋቸው እንደነበርና አሁን የሚደርስባቸው ነገርም የዚያ በቀል መሆኑን ገልጸዋል።
በማረቃ ወረዳ በማሪ አካባቢ ሰሞኑን በተነሳው የሕዝብ አመጽ ሕዝቡ በፖሊስ ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።
ዋካ የኔሰው ገብሬ ዲሞክራሲና ፍትህ በሌለበት ሁኔታ መኖር አልፈልግም በማለት ራሱን በእሳት አቃጥሎ ያጠፋበት ከተማ መሆኑ ይታወቃል።