FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, January 26, 2013

የጃኒዋሪ 23 ተከታታይ ዜና (ኤርትራ)


ከኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ
ምንጭ አሰና .ካም ራዲዮ፡
ትርጉም ጌታቸው ረዳ (www.ethiopiansemay.blogspot.com)
ከሁለት ቀን በፊት ጃኒዋሪ 21/2003 ( በኤርትራዊያኖቹ የፈረንጅኛቸው አቆጣጠር) የተቀሰቀሰው የለውጥ ንቅናቄ፤ የእንቅስቃሴው አካል ተመስሎ በመቀላቀል ያከሸፈው ሐዲሽ ኤፍሬም በተባለው መኮንን መሪነት ከሽፏል። ቢሆንም አንቅስቃሴው ተከታታይ ክትትል አንደሚያስፈልግ አሰና.ካም ራዲዮ ከአስመራ የተላለፈለት ድብቅ የዜና ዘገባ ያመለክታል።
ቀደም ብሎ የለውጥ እንቅስቃሴ መሪዎቹ የዜና ጣቢያውን ሲቆጣጠሩት በ30 ታንኮች ታጅበው ነበር ተብሎ የተዘገበው ዜና 3 ታንክ ተብሎ ይታረም። በወቅቱ እንቅስቃሴው የመሩት 100 የሚሆኑ ወታደሮች የቴ/ቪዢኑን ጣቢያ ዋና አዛዥ አስገድደው መልእክታቸው አንዲያስተላልፍ በማድረግ መልዕክታቸው በመተላለፍ ላይ እንዳለ የውስጥ ሰላቢዎች/ኢሳያስ ደጋፊዎች/ ጀኔሬተሩን በማሰናከላቸው የታቀደው መልዕክት ሙሉ በሙሉ ሳይተላለፍ ከፊሉ ብቻ ተላልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁኔታው የተደናገጠው የኢሳያስ ሥርዓት ከየቦታው ወታደሮች በብዛት በማሰባሰብ ወደ አስመራ ከተማ በማስሰረግ የንቅናቄው መሪዎች እና ወታደሮች ወደ ተቆጣጠሩበት ጣቢያ በማስከበብ ሐዲሽ ኤፍሬም በተባለ የ525ኛ ኮማንዶ አዛዥ መሪነት የሚመራው የኮማንዶ ክንፍ ከምሽቱ 2፡30 በቁጥጥር ስር አድረገውት የነበሩትን ጣቢያ ለቀው አንዲሸሹ ሆኗል። ይህ ሊሆን የቻለበትም ምክንያት፤ አስመራ ከተማን ከብቧት የነበረው ብዛት ያለው ሰራዊት “የንቅናቄው አካል” መስሎ በመጀመሪያ በማደናገሩ የንቅናቄው መሪዎቹ በዚህ ተዝናንተው እንቅስቃሴው በድንገት እንዲከሽፍባቸው ሆኗል።
ቀደም ብሎ በኢሳያስ ወታደራዊ ክፍል የአንድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበረው ንቅናቄውን የመራው ኮሎኔል ሳሊሕ ዑስማን፤የሜካናይዝድ እስታፍ ክፍለጦር ሐላፊ፤ ኰሎኔል ስዒድ ዓሊ (ቅጽል ስም ሕጃይ/ወዲ ዓሊ) እና የከባድ ብርት ብርጌድ ሐላፊ አለም መንግሥትአብ (ቅጽል ስሙ “ግዝዋ” በአማርኛ “ መርዛም ቢራቢሮ?አፍንጫ ላይ ጥቁር ጥላሸት ይምትትው”  Moth) ከከበባው በማምለጥ ተሰውረዋል።
በቶክስ ልውውጥ የተገደሉ የከባድ ብረት ተኳሽ የነበረ ‘መብራህቱ’ የተባለ እና ሌላው ከእንቅስቃሴው መሪዎች መካከል አንዱ የነበረው የረሻሽ ብርጌድ ሐላፊ የነበረው ኮሎኔል ስብሓት ለአብ ጽጌ እንደተገደለ ምንጮቻችን ገልጸዋል።የ5ኛ ክፍለ ጦር ድጋፍ ሰጪ ጦር ሐላፊ የነበረው ኮሎኔል ጸሃየ መኮንን “ወዲ ሞኬ” የተባለው ወደ ንቅናቄው መሪዎች በመጠጋት “ምን እየሆናችሁ ነው?!” በማለት ሲጠይቃቸው፤ በጥይት ተኩሰው አቁስለውት ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ ታውቋል።
ይህ ክስተት እንዲህ ሆኖም የለውጥ ፈላጊው ብዛትና በስርዓቱ ላይ እየታየ ያለው አለመርካት በከባድ ብርት ወታደራዊ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን እንቅስቃሴው በመላው ሰራዊቱ የተዳፈነ “ምሬት እና ንዴት” አሁንም እንዳለ ምንጮች የስረዳሉ። (ትርጉም ጌታቸው ረዳ)፤ (ምንጭ አሰና.ካም ራዲዮ) 1/23/2013 (ፈረንጅኛ ዘመን አቆጣጠር)።www.ethiopiansemay.blogspot.com
1/21/2013 ኤርትራ ውስጥ ስለተከሰተው አዲስ ሁኔታ ፡
ምንጭ Assenna.com ትርጉም -ጌታቸው ረዳwww.ethiopiansemay.blogspot.com
በዚህ ዜና ሦሰት ዋና ዋና የዜና ክፍሎች/ትርጉሞችን ቀርበዋል። ሁሉም በጃኒዋሪ 21 የተዘገቡ ተከታታይ ዜናዎች ናቸው።
(1)
አሰና የተባለ የኤርትራ ተቃዋሚ ድረገጽ ከአስመራ “በፌስ ቡክ” በኩል በእንግሊዚኛ ፅሑፍ የተላለፈልን ዜና ብሎ ያገኘውን  ዘገባ በትግርኛ የዘገበው ዜና ወደ አማርኛ በመተርጐም ለኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ ደምበኞቼ ያነቡት ዘንድ እንደሚከተለው ተርጉሜዋለሁ።
ኤርትራ ውስጥ ስለ ተፈጠረው አዲስ ሁኔታ ጉዳይ በፌስ ቡክ ያገኘነው ዘገባ!
ኤርትራ ውስጥ የተከሰተው ይህ አዲስ ክስተት “እንደ መፈንቅለ መንግሥት” እርምጃ ተደርጐ መተርጐም የለበትም። የእንቅስቃሴው ዋናው ዓላማ አምባገነኑን ኢሳያስ አፈወርቂ ከስልጣኑ እንዲለቅ የሚጠይቅ እና ፡ ኤርትራ ውስጥ ዲሞክራስያዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠይቅ አንቅስቃሴ ነው። ስለዚህም እንቅስቃሴው (መፈንቅለ መንግሥቱ) “ተኰላሽቷል” እየተባለ በዓለም አቀፍማሰራጫ ዜናዎችና  በኢሳያስ ተከታዮች እየተናፈሰ ያለው ወሬ  “መሰረት የሌለው” ነባራዊውን ክስተት የማይገልጽ ነው።
በዚህ መሰረት ኢሳያስን ከሥልጣኑ ለማውረድ እየተካሄደ ያለው “ውይይት/ድርድር” እንደቀጠለ ነው። (እንቅስቃሴው የዜና ማሰረጫ ማዕከሉን ከመቆጣጠር ባሻገር ያነጣጠረ ነው፡) ለወጥ ፈላጊነት ያነሳሳው  ይህ ወታደራዊው አንቅስቃሴ ፤መገናኛውን ሲቆጣጠሩ፤ ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር ከማድረግ የሚያግዳቸው አንድም ሃይል እንደሌለ ለማሳየት ያደረጉት እርምጃ እንደሆነ እና የእንቅስቃሰዉ ቡድን የሃይላቸው ግፊት ምን ያህል ብርታት አንዳላቸው  ኢሳያስ አፈወርቂን ለማሳየት ያደረጉት እርምጃም ነው። ያን ያህል እንዲራመዱ የተደረገውም ኢሳያስ ላይ ጫና ለማድረግ አንደሚችሉ ለማሳየት ያደረጉት የእንቅስቃሴ እርምጃ ነው።
ጥዋት ጥር 21 (/ጃኒዋሪ 21) የአስመራን ቴሌቪዢን ጣቢያ ተቆጣጥረውት ሲያበቁ እንደገና መደበኛ ክፍለጊዜው/ሥራው እንዲጀምር መደረጉ ይታወቃል። ሆኖም፤ ጣቢያው መደበኛ ፕሮግራሙ ቢጀምርም የእንቅስቃሴው የድክመት መመዘኛ ተደርጐ መወሰድ የለበትም።  ምክንያቱም፡ ጥዋት(21 ጃኒዋሪ) የዜና ማሰራጫ ጣቢያውን የተቆጣጠሩት እነሱ እና እንደገና መደበኛ ሥራውንም አንዲቀጥል የፈቀዱትም እነሱ እንጂ ሌላ ያስገደደዳቸው ሃይል አልነበረም። የዜና ማሰራጫ ግቢው አሁንም በቁጥጥራቸው ሥር እንዳለ ነው።
ሥራ ላይ የዋሉት የዜና ሠራተኞቹም ቢሆን ማታውኑ ወደ እየቤታቸው የሸኟቸው እነሱ ናቸው። በተጨማሪም ልክ እንደ እነዚያ የዜና ማሰራጫ ሰራተኞች ታግተው በመጨረሻ አንደተለቀቁት ሁሉ፡ታግተው የዋሉት “የአየር ሃይል” አባላትም ቢሆን በተመሳሳይ መንገድ ወደ እየቤታቸው በሰላም እንዲለቀቁ አድርገዋቸዋል።
ኢሳያስ አፈወርቂን  ከሥልጣኑ በውይይት/በድርድር ለማውረድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት የእንቅስቃሴው መሪዎች፤ ሁኔታው በሕዝብ ላይ ሰላምን የሚያናጋ ክስተት እንዳይከሰት በቆራጥነት እና በጥንቃቄ እየተራመዱ እንዳሉ ምንጮቻችን ጠቁመውናል።
እስካሁን ድረስም ከሁኔታው ጋር የተያያዘ የታሰረ ሰው/ቡድን ወይንም የተተኰሰ ጥይት አንዳልነበረም ምንጮቻችን ይጠቁማሉ።
ምንጭ Update-5 ፦Assenna.com
(2)
 የአስመራ ዋና ዋና መገናኛዎች በወታደራዊው የእንቅስቃሴ ቡድን ቁጥጥር ሆኖ ዝግ ሆነዋል።
አስመራን የተቆጣጠረው ሃይል በቁጥር አነስተኛ ሲሆን አስመራን በደጀን ከቧት የሚገኘው ሰራዊ ግን ብዙ ነው። ምንጮቻችን እንደሚገልጹት ከሆነ፡ እንቅስቃሴው በጥናት እና በተደራጀ መልኩ የታነጸ ሲሆን፤ መሪዎቹም በጥናቱ እና ባደረጃጀቱ የተማመኑ በመሆናቸው በልበ ሙሉነት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ምንጮቻችን ያመለክታሉ።
Update 3: (ከሰዓት በሗላ 21 ጥሪ 2013) ኣስመራ ከተማ በለውጥ ፈላጊ ወታደራዊ ሃይል ቁጥጥር ሥር ውላለች።
የእንቅስቃሴው መሪዎችም፡ በመከላከያ ሚኒስትሩ በስብሓት ኤፍሬም የሚመራ ሲሆን፡ ሜጀርጀነራል ፍሊፖስ ወልደዮሃንስ፡ ሜጀር ጀነራል ዑመር ጠዊል፡ ሜጀር ጀነራል ሃይለ ሳሙኤል(ቻይና) ትብብር የተካሄደ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
 በጥቆማው መሰረት ከተለያዩ ወታደራዊ የብርጌድ አዛዦች በላይ ያሉት መኰንኖች ትናት አርብ ልዩ ስብሰባ በማድረግ “በቃ! ይበቃል!” በማለት ለለውጥ መነሳት አንዳለባቸው በመነጋጋር ያደረጉት ስምምነት እንደሆነ ተጠቁሟል።
 ኣስመራን እንዲቆጣጠር የተመደበው ሰራዊት በደቡብ ኤርትራ ተመድቦ ሲሰራ የነበረ ወታደራዊ ክንፍ ነው። ይህ የለውጥ ሰራዊት ቡድን፦የዜና ማሰራጫ ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን ሌሎች የከተማው የጸጥታ ክፍሎች እና የሰራዊት አባል ሰራተኞችም በየመስርያ ቤታቸው ሰብስቦ ገለጻ አድርጐላቸዋል።  ቀሓውታ እና ማይተመናይ፡ በተባሉ የከተማዋ አካባቢዎችም የዚህ ቡድን ክፍሎች ተሰማርተውበታል።ሌሎችም እንዲሁ አስፈላጊ ቦታዎች ተሰራጭተዋል።ቤተመንግሥቱንም ተቆጣጥረውታል። ሆኖም ኢሳያስ እዛው አልተገኘም። ፎርቶ በሚገኘው በዜና ማሰራጫ ሚኒስቲር ፤ ጣቢያውና አካባቢው ልክ ጠዋት 10፡00 ሰዓት ወደ 30 የሚሆኑ  ታንኰች በመሰማራት ተቆጣጥረውታል ። ከዚህ ሌላ ነገ ኦፊሴላዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ምንጮች ይናገራሉ።
ወታደሮቹ ጣቢያውን እንደተቆጣጠሩት “የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ” ብሎ ዜና በራዲዮና በቲቪ እንዲያስተላልፍ የዜና ሚኒስትሩን ኣስመላሽ ኣብርሃን አስገድደውታል። በወቅቱ እዛው ውስጥ የሚሰሩ የሚኒሰትሩ ሰራተኞች በሙሉ ግቢው ውስጥ ከሚገኘው ፎቅ ተሰብስበው አንዲታገቱ ተደርጓል። ከተያዙት መሃልም  እዛው የዜና ሚኒስትሪ ውስጥ ተመድባ የምትሰራ  የአምባገነኑ የኢሳይያስ ኣፈወርቂ ልጅ አለችበት።፡ የአየር ማረፊያውም በቁጥጥር ሥር ነው። በዚህ ላይ የሱዳን አየር መንገድም ሁኔታው አንደተከሰተ ሰታርፍ ወደ ሱዳን አንድትመለስ ሆኗል።በንኮችም ዝግ ሆነው ውለዋል።አዲስ ዜና ሲከሰት እየተከታተልን እናሳውቃች ሸለን። Assenna.com
ትርጉም ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com

No comments:

Post a Comment