ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በንግድ ማኀበራት
ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ የ10 በመቶ የጣለው የግብር ውሳኔ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን
ኩባንያዎችና ባለአክስዮኖችን አስቆጥቷል፡፡
ባለስልጣኑ በተሻሻለው የገቢ አዋጅ ቁጥር 286/94 በአንቀጽ 4 ላይ የአክስዮን ማኀበራትና ኀላፊነቱ የተወሰነ
የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን ድርሻ ትርፍ ገቢ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው ባገኘው ገቢ ላይ የ10 በመቶ
ግብር እንደሚከፍል ይደነግጋል፡፡
ባለስልጣኑ በተሻሻለው የገቢ አዋጅ ቁጥር 286/94 በአንቀጽ 4 ላይ የአክስዮን ማኀበራትና ኀላፊነቱ የተወሰነ
የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን ድርሻ ትርፍ ገቢ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው ባገኘው ገቢ ላይ የ10 በመቶ
ግብር እንደሚከፍል ይደነግጋል፡፡
ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪ ባልተከፋፈለ
የአክስዮን ድርሻ ላይ ግብር እንዲከፈል ወስኖ ከ1ሺ461 ያህል ኩባንያዎች 816 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ
በማቀድ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ባለስልጣኑ
ለግብር ከፋዮቹ በላከው የግብር ውሳኔ መሰረት ወደኃላ ሄዶ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በሂሳብ ሚዛናቸው ላይ ለባለአክዮኖች ሳያከፋፍሉ የቆዩትን
በዓይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ ያለን ሐብት ላይ ታክስና ግብር እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡
በዚሁ የባለስልጣኑ እርምጃ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የአንድ የግል ባንክ የሕግ ባለሙያ እርምጃው አክስዮን
ማኀበራት ሥራቸውን ለማስፋፋት የሚያደርጉት ጥረት ላይ አሉታዊ ውጤት ከመጣሉም በላይ ተደራራቢ ታክስን የሚያስከትል በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አካሄድ አይደለም ብለዋል፡፡
ማኀበራት ሥራቸውን ለማስፋፋት የሚያደርጉት ጥረት ላይ አሉታዊ ውጤት ከመጣሉም በላይ ተደራራቢ ታክስን የሚያስከትል በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አካሄድ አይደለም ብለዋል፡፡
አያይዘውም በርካታ አክስዮን ማኀበራት
በአነስተኛ ካፒታል ተቋቁመው
በየዓመቱ ከሚያስመዘግቡት ትርፍ ባለአክስዮኖችን
እያስፈቀዱ ገንዘቡን ከመከፋፈል
ይልቅ ለኩባንያው ማጠናከሪያ
እንዲውል በማድረግ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲካሄድ የሚያደርጉበት
ሁኔታ እንደነበረ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ መንገድ ኩባንያዎች
ሲጠናከሩ አዳዲስ ሥራዎችን
በመክፈትና ያሉትን በማስፋፋት
ተጨማሪ የሥራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ አስተዋጽዖ ከማድረጋቸው
በተጨማሪም አዲስ በፈጠሩት
እሴት አማካኝነት ለአገር ልማት ሊውል የሚችል ታክስና ግብር የሚያስገቡበት
ሁኔታ እንዳለ አስታውሰዋል፡፡
እሳቸው የሚሰሩበትን ባንክን በምሳሌነት
በማንሳት ባለአክዮኖቹ ትርፍ ላለመከፋፈል በመወሰናቸው ባንኩ ለብድር አገልግሎት የተሻለ የፋይናንስ አቅም በማግኘቱ
ትርፋማነቱ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡የአሁኑ የገቢዎችና
ጉምሩክ ባለስልጣን ታክስና ግብር ለማስገባት ብቻ ያለመው አካሄድ ለአገር የማይጠቅምና የከፍተኛ ኩባንያዎች
ባለአክስዮኖች ሐብታቸውን ወደተጨማሪ
ኢንቨስትመንት እንዳያውሉ ተስፋ የሚያስቆርጥ
ነው ብለዋል፡፡
ከጥር ወር 2005 ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን
በባለስልጣኑ የተወሰነው ይኸው ለግብር ከፋዮች የተላከው
ማስታወቂያ
በአመዛኙ ከፍተኛ የሚባሉ ግብር ከፋዮችን ማለትም ባንኮችን፣የመጠጥና የለስላሳ
ኢንዱስትሪዎችን፣ሌሎች በአክስዮን የተመሰረቱ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን
የሚመለከት ነው፡፡እነዚህ በቁጥር አነስተኛ
የሆኑ ግን በገቢ ረገድ ከባለስልጣኑ ዓመታዊ ጠቅላላ የግብርና ታክስ ገቢ እስከ 80 በመቶ ገደማ የሚሸፍኑ
ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment