FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, January 17, 2013

የአሜሪካ ፌደራል በረራ መስሪያ ቤት በቦይንግ ድሪም ላይነር 787 አይሮፕላን ላይ ምርመራ ሊያደርግ ነው


ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌደራል መስሪያ ቤቱ ዋና ሃላፊ ሚሸል ሁሬታ  እንዳስታወቁት በአውሮፕላኑ ላይ በደረሰው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የአውሮፕላኑን ዲዛይንና አመራረቱ ምርመራ ይደረግበታል።
አውሮፕላኑ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የጃፓን አየር መንገድ ቦስተን ላይ ከቶኪዮ ተመልሶ በሚያርፍበት ሰአት እሳት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ባለፈው አርብ የጃፓን ኦል ኒፖን አየር መንገድ ሪፖርት እንዳደረገው በሚበርበት ሰአት በፓይለቱ በኩል ያለው መስኮት በመሰንጠቁ የመመለሻ በረራውን ለመሰረዝ ተገዷል።
ይኸው አየር መንገድ  ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን በሞተሩ ውስጥ ዘይት በማፍሰሱ በረራውን ለማቋረጥ ተገዶ እንደነበርና የፍሬን ችግርም በማጋጠሙም ከያማጉቺ ወደ ቶኪዮ ያደርግ የነበረውን በረራ መሰረዙን ገልፆአል። እንዲሁም አውሮፕላኑ  151  ሊትር የሚሆን ነዳጅ በማፍሰሱ ምክንያት ማክሰኞ ከቦስተን ወደ ቶኪዮ ያደርግ የነበረውን በረራ ኣቋርጧል።
ባለፈው አመት በዩናይትድ ኤይር ላይንስ በተፈጠረ የኤሌክትሪክ ችግር ምክንያት አውሮፕላኑ በድንገት እንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን የካታር አየር መንገድም በዲሴምበር ወር አንዱ አውሮፕላኑ በደረሰበት የቴክኒክና የኤሌክትሪክ ችግር ምክኒያት ከበረራ እንዲቆም አድርጎታል የቦይንግ ካምፓኒ በሰጠው መግለጫ የአውሮፕላኑ ዲዛይን አስተማማኝና ለበረራም ከአደጋ ነፃ የሆነ ነው ብሎታል።
ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን  የተሰራው ካርቦን ከተባለውንጥረ ነገር ሲሆን በቴክኖሎጂም እጅግ ዘመናዊ የተባለለት ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ የመጀመሪያ በመሆን 10 ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላኖችን ከቦይንግ የገዛ ሲሆን ባለፈው ነሐሤ የመጀመሪያውን አውሮፕላን ተረክቦ ወደ ሃገር ቤት በከፍተኛ የአቀባበል ስነስርአት አስገብቷል።
በገበያ ላይ ውሎ ውጤቱ ያልተመሰከረለትን አዲስ አውሮፕላን መግዛት ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል በሞያው ላይ የተሰማሩ የኤሮኖቲክ ኢንጅነሮች ያስጠነቅቃሉ።

No comments:

Post a Comment