FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, January 25, 2013

አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ራሱዋን መስቀሉዋ ተዘገበ


ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኩዌት በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ራሷን በገመድ በመስቀል አረብ ታይምስ በፎቶግራፍ አስደግፎ ያወጣው ዘገባ ያመለክታል።
የጸጥታ ሀይሎች በአካባቢው ሲደርሱ ስሟ  ያልተጠቀሰው ኢትዮጵያዊት ራሱዋን አንቃ መግደሉዋ ለመመልከት መቻላቸውን በዘገባው ተመልክቷል። የልጂቱ አስከሬን ለምርመራ መወሰዱ ቢታወቅም፣ ሰራተኛዋ ራሱዋን ማጥፋቱዋንና አለማጥፋቱን የኩዌት የደህንነት ሰራተኞች ከገለጹት ውጭ በሌላ ወገን የተረጋገጠ ነገር የለም። የኢትዮጵያ ኢምባሲም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።
በአረብ አገራት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው በደል እየጨመረ ቢመጣም ፣ ወደ አገራቱ የሚሄደው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ሊቀንስ አልቻለም። ባለፈው አመት ብቻ በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲ አረብያ የተጓዙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ160 ሺ በላይ ነው።

No comments:

Post a Comment