FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 23, 2013

በአለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰቃየ የለም ያሉት አቶ ስብሀት ነጋ ዛሬ ያ ሁኔታ መቀየሩን ገለጡ


ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- አንዱ ጠግቦ ሲያድር ያልጠገበው ደግሞ በሰላም ተኝቶ ያድራል ብለዋል::
አዲስ አበባ ለሚታተመው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ከቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) መሪ የነበሩትና ዛሬ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ተጽዕኖቸው እየበረታ መሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስብሀት ነጋ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ወዲህ ሚዲያ ላይ በብዛት እየቀረቡ መገኘታቸውን በዚህም ለኢሳት ጭምር ቃለ ምልልስ የሰጡበትን ሁኔታን አስታውሰዋል::
“ከመለስ መታመም ጀምሮ ሚዲያውን ለምን አበዛኸው ካልሆነ በቀር እኔ ከሚዲያ አልተለየሁም ፣ ፓል ቶክ የሚባል አለ ፣ በቪ ኦ ኤም ተሳትፌአለሁ፣ ለኢሳት እንኳን ቃለ ምልልስ ሰጥቻለሁ፣ ደውለውልኝ ቃለ ምልልስ ሰጥቻለሁ” ብለዋል::
ከአቶ መለስ ማለፍ በኋላ ተጽዕኗቸው እየበረታ ስለመምጣቱ ለተነሳላቸው ጥያቄ ማስተባበያ የሰጡት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝን ካገኟቸው ሁለት አመት እንዳለፋቸው ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን  አጭር ይሁኑ ረዥም ጨርሰው እንደማያውቋቸው አብራርተዋል::
እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በአለም የተሰቃየ ህዝብ ያለ አይመስለኝም፣ ይፈጠራል፣ ራቁቱን ይሞታል፣ ከተፈለገም ይገደላል” በማለት መናገራቸውን ተከትሎ ዛሬ ይህ ቀርቷል ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ስብሀት አሁን ያመጸ ህዝብ የለም፣ ተወልዶ ወደ ውትድርና ሂድ የሚል የለም ፣ ቀይ ሽብር የለም ፣ አንድ ዩኒቨርሲቲ ነበረን አሁን 32 ዩኒቨርሲቲ አለን ፣ አንዱ ጠግቦ ያድራል ባይጠግብም ተኝቶ ያድራል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል:፡ ዛሬ የሚያለቅሱት ወላጅ አልባ የሆኑት የአፄ ሀይለስላሴ ስርአት ናፋቂዎች ፣ ኢሰፓዎች ፣ ኢህአታ እና መኤሶኖች ናቸው ሲሉ ፈርጀዋል::
በግምቦት 1981 በኮሌኔል መንግስቱ ሀ/ማርያም ላይ በተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በሻቢያ በኩል ተባባሪነታችንን ተጠይቀው በህውሀት በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን አስታውሰዋል::
” በ1981 ግንቦት ወር በመፈንቅለ መንግስት መንግስቱ ሀ/ማሪያምን ለመገልበጥ የሞከሩት፣ ሻቢያን ላኩብን፣ ልንገለብጠው ነው ብለው ፣ መንግስቱ በግል ቢገለበጥ ባይገለበጥ ስርአቱ ካልተለወጠ ብለን ትግላችንን ቀጠልን እንጂ አላገኘናቸውም:: በማለት ሻቢያ ጭምር ለመተባበር የፈቀደውን ሂደት ህወሀት አለመቀበሉን አብራርተዋል::
አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ችሎታ ያንሳቸዋል በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ መለስም ከምክትሎቹ ከነ ተፈራ ዋልዋ፣ ከነ ዶ/ር ካሱ ኢላላ ነው ችሎታውን ያዳበረው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::

No comments:

Post a Comment