FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, January 26, 2013

አዲስ ታይምስ መጽሄት ገበያ ላይ አለመዋሉ ታወቀ


ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይዘጋጅ የነበረውና ከ1997 ዓም ወዲህ ከታተሙት የግል ጋዜጦች መካከል በጠንካራ ዘገባዎቹ እና በአንባቢ ብዛቱ ቀዳሚ የነበረው ፍትህ ጋዜጣ በመንግስት ጫና ከተዘጋበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ይዘጋጅ የነበረው አዲስ ታይምስ መጽሄት በገዢው ፓርቲ በደረሰበት ጫና ዛሬ ለንባብ አለመብቃቱ ታውቋል።
በአራት ኪሎ ፣ ስድስት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ፍላሚንጎ ፣ ቦሌ እና ካዛንችስ አካባቢዎች ተዘዋውሮ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አንባቢዎች በመጽሄቷ አለመውጣት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
ካዛንችስ ዴንቨር ካፌ ቡና እየጠጡ መጽሄቷን ጠይቀው ማጣታቸውን የገለጹ አንድ ጎልማሳ የአገራችንን ፖለቲካ እና አጠቃላይ ሁኔታ የምንረዳበት መጽሄት ዛሬ አልወጣችም፣ እንግዲህ ይህን ጉድለታችንን የትኛው ሚዲያ ሊሞላው ነው ኢቲቪ ይሆን ሲሉ ተሳልቀዋል።
ዘጋቢያችን የመጽሄቷን አዘጋጆችና እና የስራ ባልደረቦችን ለማነጋገር ቢሞክርም ሁሉም ስልካቸው ከአገልግሎት ውጭ በመሆኑ በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም።
ዘጋቢያችን ከመንግስት የዜና ምንጮች እንዳጣራው መጽሄቱ ለህትመት ያልበቃው የብሮድ ካስት ኤጀንሲ መጽሄቱ አመታዊ እድሳት እንዲያደርግ ባለመፍቀዱና ሳንካ በመፍጠሩ ነው።
አዲስ ታይምስ መጽሄት ቀደም ሲል ከነበረበት ከ3 ሺ ቅጅዎች ወደ 40 ሺ ቅጅዎች ከፍ ብሎ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።
የአቶ መለስን ራእይ እናስፈጽማለን የሚለው የሀይለማርያም ደሳለኝ መንግስት፣ ጋዜጦችን በማፈን ራእዩን በትክክል እየተገበረ መሆኑን አንባቢዎች ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment