ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እየተባለ የሚጠራውን ክፍል በስራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብዱል ጀባር ሀሚድን ከስራ ያባረረው የአየር መንገዱ ሙስሊም ሰራተኞች ከሌሎች ወገኖች ጎን ተቀላቅለው ተቃውአቸውን እንዲገልጹ አደራጅቷል በሚል ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
በተያየዘ ዜናም በሱፐርቫይዘርነት ደረጃ ስትሰራ የነበረችው ትእግስት ደምሴ ከስራ በተቀነሰ ሰራተኛ ላይ የሀሰት ምስክርነት እንድትሰጥ ተጠይቃ ፈቃደኛ ባለመሆኗ መሆኑ ታውቋል።
ኢሳት የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ 50 የአየር መንገዱ ሰራተኞች መባረራቸውንና በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት መተካታቸውን ገልጾ ነበር። ከስራ የተቀነሱት የ36 ሰራተኛች ሙሉ ስም ዝርዝር እና አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሰን ሲሆን፣ ሙሉውን ዝርዝር በኢሳት ዌብሳይት ላይ ታትሞ መውጣቱን ለመግልጽ እንወዳለን።
በጉዳዩ ዙሪያ የአየር መንገዱን አመራሮች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment