FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 23, 2013

የአፍሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ካፍ ኢትዮጵያን 10 000 የአሜሪካ ዶላር መቅጣቱን አስታወቀ


ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ካፍ ኢትዮጵያን 10 000 የአሜሪካ ዶላር መቅጣቱን አስታወቀ:: ሳላሀዲን ሰኢድ ከዛምቢያ ጋር በተደረገው የመጀመሪያ ግጥሚያ ምርጥ ተጫዋች ተባለ::
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ግጥሚያ ደጋፊው ህዝብ የተለያዩ ነገሮችን ወደ ሜዳው በመወርወር በዛምቢያ ቡድን ላይ ላሳየው ተቀባይነት የሌለው ተቃውሞ ቅጣቱ መጣሉን ቢቢሲ አመልክቷል::
በደቡብ አፍሪካ ቅዳሜ እለት በሁለቱ ቡድኖች መካከል በተደረገው ጨዋታ በረኛው ጀማል ጣሰው በቀይ እንዲወጣ ዳኛው ከወሰኑ በኋላ ነበር በስታዲየሙ የሚገኘው ደጋፊ የተለያዩ ነገሮችን ወደ ኳስ ሜዳው በመወርወር ቁጣውን የገለጸው::
በዚህ የተነሳ ካፍ በኢትዮጵያ ላይ 10 000 የአሜሪካ ዶላር ቅጣት የወሰነ ሲሆን ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ላይ ባለመገኘቷ የቅጣቱ ግማሽ እንደሚነሳላት ከቢቢሲ ዘገባ ለመረዳት ተችሏል::
በረኛው ጀማል ጣሰው በካፍ ህግ መሰረት ከዛምቢያ ጋር የተደረውን ጨዋታ ጨምሮ በሁለት ጨዋታዎች እንዳይሳተፍ መቀጣቱ ይታወቃል::
ይህ በዚ ሳለ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ ሳላሀዲን ሰኢድ የጨዋታው ኮከብ ተሰኝቶ የኦሬንጅ ካፕ ተሸላሚ ሆኗል::
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በየግጥሚያው ምርጥ ተጨዋች ተመርጦ የኦሬንጅ ካፕ ተሸላሚ የሚሆን ሲሆን ሳላሀዲን ሰኢድም ይህንኑ ሽልማት ነው ያገኘው::

No comments:

Post a Comment