FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, January 26, 2013

የኢሳት ቀን በሳንድሽን ኖርዌይ ካምፕ ውስጥ ተከበረ


ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ተነሳሽነት ስለ ኢሳት አላማ ለኖርዌጅያን ማህበረሰብ ፣ በ ሳንድሽን አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ ለማሳውቅ እና ኢሳትንም እንዲደግፉ ለማድረግ የኢሳት ቀን በሚል ያዘጋጁት በአል መከበሩን ገልጸዋል።
በእለቱም በሳንድሽን ለሚኖሩ ኖርዌጅያን የተለያዩ የፖለቲካ ተወካዮች ፣ የስደተኞች አስተማሪዎች በሙሉ ስለ ኢሳት የሚገልጽ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት እንዲያውቁ ፣ በኢሳት ቀን ፕሮግራም እንዲገኙ፣ እና እንዲደግፉ መደረጉን ገልጸዋል።
እኤአ ጃንዋሪ 24 ቀን 2013 በተከበረው በአል ላይ ለተገኙት በሙሉ ስለ ኢሳት ገለጻ መካሄዱን ኢትዮጵያውያኑ በላኩት ዘገባ አመልክተዋል።

No comments:

Post a Comment