FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, January 21, 2013

ልዩ ሀይል በአላጣማ መግባቱን ተከትሎ በከተማው ያለው ውጥረት አይሏል


ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻ /  
ኢሳት ዜና:- የኢሳት የአላማጣ ምንጮች እንደተናገሩት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰአት አካባቢ ከመቀሌ የተነሱ በ3 መኪኖች የተጫኑ ልዩ የፌደራል ፖሊስ አባላት አላማጣ በመግባት ህዝቡን እያሸበሩት ነው።
በከተማዋ ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው  አካባቢ የሚገኙ 200 የሚጠጉ የቤት ባለንብረቶች ንብረቶቻቸውን ነገ ማክሰኞ የማያወጡ ከሆነ ፣ ቤቶቻቸው በዶዘሮች እንደሚፈርሱ ንብረቶቻቸውም እንደሚወረሱ እንደተነገራቸው ታውቋል። ልዩ የፖሊስ ሀይላትም ተቃውሞ ሊያነሱ ይችላሉ ብለው የሚጠሩዋቸውን አካባቢዎች እያሰሱ ሲያስጠነቅቁ አምሽተዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ይፈርሳሉ ተብለው የተመዘገቡት ቤቶች 2 ሺ ናቸው።
“ከፍተኛ ውጥረት አለ፣ ልዩ ሀይሎች ህዝቡን እያሸበሩት ነው፣ በነገው እለት ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል፣ በከተማዋ ሁለት ሶስት ሆኖ ማውራት አይቻልም”  በማለት አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።
ባለፈው ጥር መግቢያ ላይ በከተማዋ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ ተይዘው የታሰሩ የከተማ ታዋቂ ሰዎች እስካሁን አለመፈታታቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በክብሮም አሰፋ ሞላ የተጻፈው “የራያ ህዝብ ባህልና ታሪክ ” መጽሀፍ እንዳይሸጥ ተከልክሎአል። መፅሀፉ ለምን እንዳይሸጥ እንደተከለከለ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም አንዳንድ ወገኖች እንደጠቆሙት መጽሀፉ ህወሀት ስለራያ ህዝብ ማንነትና ታሪክ ከሚሰጠው ትንተና ጋር የሚቃረኑ ትንታኔዎችን ይዟል።

No comments:

Post a Comment