FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, January 27, 2013

የአለም አቀፉን መገናኛ ብዙሃን የሳበው የዘይኒ ከድርና የኮንትራት ሰራተኞቻችን ሰቆቃ !

የማለዳ ወግ . . . የአለም አቀፉን መገናኛ ብዙሃን የሳበው የዘይኒ ከድርና የኮንትራት ሰራተኞቻችን ሰቆቃ !
የ19 አመቷ ዘይኒ ከርድ በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲ ከሚመጡት እልፍ አእላፍ የኮንትራት ሰራተኞ እህቶች ውስጥ አንዷ ናት ፡፡ አርሶ አደር ገበሬ ቤተሰቦችዋ ተበድረውና ተቀድመው 6.000 ብር በማውጣት በኮንትራት ስራ ውል ወደ ሳውዲ አረቢያ እንድትሄድ አደረጉ፡፡ በአጭር ጊዜ ልዩነት ወደ ሳውዲ ምስራቃዊ ክፍል ወደ ደምማም በሰላም የገባችው ዜይኒ በአሰሪዎችዋ ቤት ብትገባም እንደታሰበው ስራን ሰርታ ድሃ ወገኖችዋን መደገፍ የሚያስችላት የሰመረ ስራና ህይዎት አልጠበቃትም ፡፡ የስራው ብዛት እንግልቱ ሳያንስ ማንጓጠጡና መደብደቡ አስመረራት ፡፡ እናም ለማለዳው የፈጅር ጸሎት የተከፈተውን የአሰሪዎችዋን በር ተጠቅማ በመጥፋት በኮንትራት ወደ አስመጧት አሰሪና ሰራተኛ አገናኞች ቢሮ ተጠጋች፡፡ ከዚያም እንደእርሷ ያልጠበቁት የገጠማቸውን በርካታ ተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኛ እህቶችን ተቀላቀለች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ደግሞ በመጣ እግሯ ወደ ሃገር ቤት ተመለሰች፡፡ ከአዲስ አበባ ሁለት አውቶቡስ ይዛና የሶስት ሰአታትን በእግሯ በመጓዝ ከችግር ታወጣናለች ብለው የላኳትን አርሶ አደር ገበሬዎች ባዶ እጇን ትቀላቀለቸው ዘንድ ግን ሆነ . . . ቅንጫቢ የዚህች ጉብል ህይዎት በወጌ ይዳሰሳል ! ዛሬ ትመለከቱት ዘንድ ታዋቂው Bloomberg የብሎምበር ዜና አውታር ያሰራጨውን የዘይኒ ከድር እና የቤተሰቦቿ እጣ ፈንታ እነሆ ! ይህ አሳዛኝ የኮንትራት ሰራተኛዋ ታሪክ የዘይኒ ብቻ አይደለም ! የዜና አውታሩ ትኩረት የሰጠውን ስሙና እዩት ብየ እንጂ በእጀ ላይ የሚገኙ አሳዛኝ የከልታማ እህቶቻችን አስከፊ ህይዎት አቅም በፈቀደ መጠን እለቃቸዋለሁ፡፡ በህጋዊ የኮንትራት ስራ መጥተው በደመወዝ አለመቀበል ፤ በስራ ብዛት ፤ በአስገድዶ መደፈር፤ ለውስጥ ደዌ በሽታ የተዳረጉትንና ያበዱትን እህቶች ለማየት ከፈለጉ ወደ ጅዳና ሪያድ መጠለያዎች ጎራ ማለት ይበቃል ! መዳረሻቸው ሳይታወቅ የቀሩትማ የትየለሌ ናቸው ! የመንግስት ሃላፊዎች አያዩም አይሰሙም አይባልም ፤ ያያሉ ይሰማሉ ! መንግስት አያይም አይሰማም አይባልም ፤ ያያል ይሰማል! ህዝብ አያይም አይሰማም አይባልም ፤ ያያል ይሰማል ! . . .በዜጋ ላይ ሰቆቃ ሲደርስ ካልደረስን ፤ስለ መልክአ ምድሩና ስለ ባንዲራው ብንምል ብንገዘትና ብናለቅስ ሰብዕና ሲገፈፍና የዚያች ምድርና የባንዲራው ባለቤቶች ሲገፉ ድምጻችንን በህብረት ማሰማቱ እንዴት ይገደናል ? ሃገርና ባንዲራን መውደድ ብቻውን ምን ያደርግልናል ! ? አረ በባንዲራው አንድ እንበል !
ቸር ያሰማን . . .
ነቢዩ ሲራክ

No comments:

Post a Comment