FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, January 18, 2013

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድ ነን አንከፋፈልም አሉ


ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “አንድነን አንከፋፈልም” በማለት የሰደቃና የአንድነት ፕሮግራም አዘጋጅተው ውለዋል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተካሄደው የሰደቃና የአንድነት ስነስርአት ላይ ተካፍለዋል። ድርጊቱ ገዢው ፓርቲ ሙስሊሞችን ለሁለት ለመክፈል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም የታለመ መሆኑን በስነስርአቱ ላይ የተካፈሉ ሙስሊሞች ገልጸዋል።
ተመሳሳይ ዝግጅቶች በሻሸመኔ፣ በጅማ እና በመቱ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ካለፈው  አመት ጀምሮ ድምጻችን ይሰማ በማለት ተቃውሞአቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
በመንግስት በኩል የተያዘው ፖሊሲ ” በትግስት እንያቸው” የሚል መሆኑን አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ተናግረዋል። ሙስሊሞቹ “ተቃውአቸውን ከጊዜ መርዘምና ከመሰላቸት አንጻር ያቆማሉ ተብሎ በመንግስት የተያዘው እሳቤ ትክክል አለመሆኑን በየሳምንቱ በሚደረጉ ተቃውሞዎች እንዲሁም መንግስት ሙስሊሙን በመክፈል እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ በሚያደርገው እንቅስቃሴ መረዳት ይቻላል ” በማለት አንድ የእምነቱ አስተማሪ ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።

    No comments:

    Post a Comment