FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, January 31, 2013

ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል / በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ ራሱዋን መጸዳጃ ውስጥ በመግባት አጠፋች


ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ቀጠሮ ሰጥቷል።
የችሎቱ ዳኛ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እና አሳታሚው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ማስተዋል ብርሀኑ መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ ብይኑን ለመስጠት ለየካቲት አንድ ቀጠሮ ሰጥተዋል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች በችሎቱ ላይ አልተገኙም። በችሎቱ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የጋዜጠኛው ቤተሰቦች፣ አድናቂዎችና ስራ ባልደረቦች ተገኝተዋል።


በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ ራሱዋን መጸዳጃ ውስጥ በመግባት አጠፋች

ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ገነቴ ጌታቸው የተባለችው ተማሪ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ራሱዋን በመወርወር ያጠፋቸው ባለፈው ሳምንት ነው። በትምህርቷ ከፍተኛ ውጤት የነበራት ተማሪ ገነቴ ራሱን  ለማጥፋት ለምን እንደወሰነች በትክክል ለማወቅ ባይቻልም ተማሪዎች እንደሚሉት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው ተማሪዎች የውሀ፣ የመጸዳጃ እና ሌሎች አገልግሎቶች አልተሟሉልንም በሚል ተቃውሞ ከማስነሳታቸው ጋር ሊያያዝ  ይችላል። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸውን በማስቸገር በሚላክላቸው ገንዘብ የፕላስቲክ ውሀ  ሲገዙ መቆየታቸውን ያወሱት የሟቿ ባልደረቦች፣ ይሁን እንጅ ተማሪዋ የመጣችበት ቤተሰብ ይህን ለሟሟላት ባለመቻሉ ተማሪዋ በችግር ውስጥ ትገኝ ነበር ብለዋል። አሟሟቷንም ከገንዘብ ችግር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ትምህርታቸውን አቁመው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ግቢያቸው ተመልሰው መደበኛ ትምህርት የጀመሩ ቢሆንም፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግን አሁንም በዩኒቨርስቲው አካባቢ በብዛት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪዎችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment