FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, January 17, 2013

የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ


ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- እንደ ቢቢሲ ዘገባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲሱ ቦይንግ ድሪምላይነር ለጊዜው አገልግሎት እንዳይሰጥ በአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣን ታግዷል።
 በመላው ዓለም ላይ 50 የሚሆኑ ቦይንግ ድሪም ላይነር እንዳሉ ያመለከተው የዜና አውታሩ ዘገባ፤የቴክኒክ ፍተሻ እስኪደረግ ድረስ የሁሉም አገራት ቦይንግ ድሪምላይነር ፍላግሺፖች አገልግሎታቸውን እንዲያቆሙ የዩ.ኤስ ፌዴራል አቪዬሽን አሳስቧል።
 አዲሱ ድሪም ላይነር ነዳጅ የመትፋት፣ የኮክ ፒት መስኮት መሰንጠቅ፣ የፍሬን እና የኤሌክትሪክ ብልጭታ የመፍጠርችግር እንደተስተዋለበትም ተገልጿል።
 የአውሮፕላኑ "ሊትየም አዮን ባትሪ" የፍተሻው ዋነኛ ትኩረት መሆኑም ተመልክቷል።
ትናንት ረቡዕ በጃፓን  ቦይንግ ድሪም ላይነር ላይ የባትሪ ችግር አጋጥሞ አውሮፕላኑ ባስቸኳይ እንዲያርፍ መደረጉን "ኦል ኒፖን ኤር ዌይስ"የተሰኘው የጃፓን አየር መንገድ ሪፖርት አድርጓል።
በዓለም ላይ ቦይንግ ድሪም ላይነርን የሚጠቀሙ ስምንቱም አየር መንገዶች በዩ.ኤስ አቪዬሽን ማሳሰቢያ መሰረት አገልግሎቱን ማቆማቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
እነሱም የጃፓን፣የአሜሪካ፣የቺሊ፣ የህንድ፣የኩዋታር፣የፖላንድና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች ናቸው።
በብድር 10 ቦይንግ ድሪም ላይነር የገዛችው ኢትዮጵያ፤ ከአፍሪካ ብቸኛዋ የድሪም ላይነር ባለቤት ነች።
አውሮፕላኖቹ አዲስ አበባ ሲገቡ ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደነበር ይታወሳል።
 የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የጃፓን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ላይ ያጋጠመው የቴክኒክ ችግር በኢትዮጵያዎቹ ላይ አውሮፕላኖች ላይ አለመከሰቱን ገልጾ፣ ለጥንቃቄና ለደህንነት ሲባል ላልተወሰነ ጊዜ በረራ ማቋረጡን ዘግይቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment