FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, January 19, 2013

በቦረና ዞን ህዝቡ ለሚሊሻ ማደራጃ ገንዘብ እንዲያወጣ እየተገደደ ነው


ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መንግስት የአካባቢ ሚሊሻ ለማቋቋም በሚል ምክንያት እያንዳንዱ ዞኑ ነዋሪ 70 ብር በነፍስ ወከፍ እንዲከፍል አዟል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ” እኛን መልሶ ለሚበድለን ሚሊሺያ እንዴት ገንዘብ እናዋጣለን” በሚል ተቃውሞውን በማሰማቱ እስካሁን ድረስ፣ በቂ መዋጮ ሊዋጣ እንዳልቻለ ታውቋል።
መንግስት በዞኑ እየተባባሰ የመጣውን ከብሄር ጋር በተያያዘ የሚነሳውን ግጭት ለማስቆም ባለመቻሉ በሶማሊ ክልል እንደተደረገው የአካባቢ ሚሊሺያ ለማቋቋም ማቀዱ ታውቋል።
ነዋሪዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ የተገደዱት ለሚሊሺያዎቹ ማሰልጠኛ  ነው።
በቦረና ዞን በሶማሊ እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል በተደጋጋሚ የሚታየው ግጭት በየአመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። በአካባቢው ለሚታየው ግጭት ምክንያቱ የመንግስት የዘር ፖሊሲ ነው በማለት የአካባቢውን ነዋሪዎች አነጋግሮ ኢሳት አንድ ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment