FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 30, 2013

ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት የህትመት ዋጋ ጭማሪ አደረገ


ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-በማሽኖች እርጅናና በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ውስጥ የሚዋልለው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጦች የሕትመት ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፡፡

ማተሚያ ቤቱ በተለይ ባለቀለም ጋዜጦችን ተቀብሎ የማተም አቅሙ ከጊዜ ወደግዜ እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር
ተያይዞ ብዙ ጋዜጦችን በወቅቱ ማተም ባለመቻሉ በተለይ ቅዳሜ እና እሁድ የሚወጡ ጋዜጦች _ማለትም
ሪፖርተር፣ፎርቹን፣ካፒታል ጋዜጦች ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ መዳረጋቸው ተመልክቷል ፡፡

በደካማ አገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ የሚዳክረው ይኸው ማተሚያ ቤት ባለፈው ሳምንት በድንገት እስከ 12 በመቶ
የሚደርስ ጭማሪ በጋዜጦች የህትመት ዋጋ ላይ አድርጓል፡፡ ጭማሪው በተለይ ወትሮውም ከእጅ ወደአፍ ገቢ
ያላቸውን ጋዜጦች በፍጥነት ከገበያ ሊያስወጣ ይችላል የሚል ግምት አሳድሮአል፡፡

ማተሚያ ቤቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የዋጋ ጭማሪ ሲያደርግ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡ይህን ተከትሎም
እንደሪፖርተር ያሉ ጋዜጦች መሸጫ ዋጋ 10 ብር መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

ማተሚያ ቤቱ የህትመት ሥራ ውል ከጋዜጦች አሳታሚዎች ጋር ለመዋዋል ረቂቅ ሕግ አዘጋጅቶ በአሳታሚዎች
ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞት ሥራ ላይ እንዳይውል ከተደረገ ወዲህ እንደፍትህእናፍኖተ ነጻነትያሉ ጋዜጦችን
ከሕግና ከሥርዓት ውጪ አላትምም ከማለት ጀምሮ እያተማቸው ያሉ ጋዜጦችን ብዙውን ጊዜ በማሽን ብልሽት
በማሳበብ በሰዓቱ ወጥተው እንዳይሰራጩ እንቅፋት በመሆን ለኪሳራና ለአላስፈላጊ ወጪ በመዳረግ ላይ እንደሚገኝ
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ገልጸዋል፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የፕሬስ ነጻነት በተግባር እንዳይረጋገጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ከፍተኛ ጥረት
በሚያደርግበት በዚህ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ የሚታተሙ የፍቅርና የኪነጥበብ መጽሔቶች ሳይቀር ጭልጥ ብለው
የፖለቲካ ጉዳዮችን ከማስተናገድ አልፈው የሕትመት መውጫ ጊዜያቸው ከወር ወደ 15 እና ሳምንት ዝቅ እያደረጉ
መምጣት፣የነፍስ ወከፍ ኮፒያቸውም ከጋዜጦቹ በሚያስከነዳ መልኩ በአማካይ እስከ 30 መድረሱ ሌላ ራስምታት
እንደሆነበት ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡

ታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ባልደረቦቹ  የሚያዘጋጁት አዲስ ታይምስ መጽሄት ባለፈው ቅዳሜ ሳይወጣ
መቅረቱን መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment