FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, January 17, 2013

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ልትሆን እንደምትችል ተጠቆመ


ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የህብረቱ ሊቀ-መንበር ለማድረግ ኢትዮጵያ ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ ጥረት ስታደርግ መቆየቷ ተገልጿል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ኢታዮጵያ በመጪው ሳምንት 20ኛውን የ አፍሪካ ጉባኤ ታስተናግዳለች።
ከህብረቱ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር ተጣምሮ ይካሄዳል በተባለው በዚህ ጉባኤ ላይ፤የሁለቱ ሱዳኖች ፣ የሶማሊያ ፣ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎና የሰሞኑ የማሊ ሁኔታ አበይት ትኩረት አግኝተው ይመከርባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ።
በጉባኤው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የወቅቱ ሊቀመንበርነትንም ስፍራ ቤኒን ለባለተራው አገር ታስረክባለች።
እንደ አምባሳደሩ ገለፃ የሊቀመንበርነቱ ተራ የምስራቅ አፍሪካ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ይህን ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ጥረቶችን ስታደርግ ቆይታለች።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከአንድ የውጪ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆኖ የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment