FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, January 28, 2013

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነቱን ወሰደች


ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ለመጪው አንድ ዓመት የአፍሪካ ህብረትን በሊቀ-መንበርነትን እንዲመሩ ተመረጡ።
እሁድ አዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የመሪዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ከቤኒን መረከቧን የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል።
ይህን ታላቅ ድርጅት ለመጪው አንድ ዓመት እንድመራ በመመረጤ ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል-አቶ ሀይለማርያም።
"ሹመቱንም የምቀበለው በታላቅ አክብሮትና የደስታ ስሜት ነው" ሲሉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን የአንድ ዓመት የሊቀመንበርነት ጊዜ ከቤኒን ለመረከብ ፍላጎቷን ያሳየችው ከሳምንታት በፊት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በሰጠችው መግለጫ ነው።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ "የሊቀ-መንበርነቱ ተረኛ ኢትዮጵያ ነች" በማለት ቀደም ብለው የሰጡት መግለጫ፤በህብረቱ አባል አገራት ዘንድ-"የህብረቱን ፕሮቶኮል ያላከበረ"ነው የሚል ትችት ማስከተሉ ይታወሳል።
ትችት የሰነዘሩት አባል አገራት ፤ኢትዮጵያ ሊቀመንበርነቱን ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየችው ተራዋ ሆኖ ሳይሆን ህብረቱ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ የሚያከብርበት ስለሆነ ሹመቱ ከዚያ ጋር እንዲገጣጠምላት በማሰብ ነው ባይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment