FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, January 19, 2013

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሽን 70 በመቶው የአመራር ቦታ በህወሀት አባለት የተያዘ ነው ተባለ


ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ሁለተኛ ጥናቱ ላይ እንዳመለከተው በ11 መምሪያዎች የተዋቀረው በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተዳደርው የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂኔሪንግ ኮርፓሬሽን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ ኢንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይሬክትርነት የሚመሩ በ29 የከፍተኛ አመራር አባላት ነው።
ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ የህወሀት አባላት የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያንዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም ሰዉ የለም ፣ እንደጥናቱ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ኢንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት ኢንጂኔሪንግ ኮርፓሬሽን በሲቪልና ወታደራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙ የጠቀሰው ግንቦት7፣ ከአስራ ሦስቱ ኢንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተዳድሩት የህወሀት አባላት ናቸዉ። በኮርፖሬሽኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የህወሀት አባላት መካከል ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ  የብረታ ብረት ኢንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይሬክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮጀክቶች አስተዳደር ሀላፊ፤ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ልማት ዳይሬክተርና  ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይሬክተር ይገኙበታል።
ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት ኢንጂኔሪንግ ኮርፓሬሽን ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ናቸው። ኬሚካልና ሴንተቲክ ኢንዱስትሪ ሃላፊ መ/አ ሰለሞን ዘውዴ፣ አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሃላፊ ኮ/ል ፍሰሀ ግደይ፣ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ሃላፊ ሻለቃ መኮንን በላይ፣ ፓወር ኢንዱስትሪ ሃላፊ፣ ሻምበል አሰፋ ዮሀንስ፣ ሆሚቹ ኢሚዩኔሽን ኢንጂነሪንግ ሃላፊ ኮ/ል ሀድጉ በላይ፣ ህብረት ማሽን ቱል ኢንጂነሪንግ ሃላፊ፣ ሻምበል ተሰማ ግደይ፣ ቢሾፍቱ አቶሞቲቭ ሎኮሞቲቭ ሀላፊ፣ ኮ/ል ገብረመድህን ገ ስላሴ ፣ የደጀን አቪየሽን ኢንዱስትሪ ሀላፊ ሳለቃ ኢሉ ጸጋየ እንዲሁም የጋፋት አርማመንት ኢንዱስትሪ ሀላፊ ሻለቃ ግሩም ገብረመድህን የህወሀት አባላት ትጋራይ ተወላጆች መሆናቸው በጥናቱ ተመልክቷል። የኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ሃላፊ አቶ ጋሻው እምሩ፣ እርሻ መሳሪያዎች ኢንዱስትሪ ሃላፊ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ እና የሀይቴክ ኢንዱሰትሪ ሀላፊ ኮ/ል ጸጋየ አንሙት የአማራ ተወላጆች ሲሆኑ፣ ከኦሮሞ ደግሞ የፋብሪኬንና ስትራክቸራል ኢንዱስትሪ ሀላፊው ኮ/ል ብቂላ ብቻ ተጠቅሰዋል።
ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ መሆኑን ተጠቅሷል። ግንቦት7 በቅርቡ በኢትዮቴልኮም ውስጥ ያለውን የብሄር ተዋጽኦ ይፋ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሰዎቹ የሚሾሙት በዘራቸው ሳይሆን በችሎታቸው ነው በማለት ይከራከራል። መንግስት 7ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን 200 ሚሊዮን ብር በማውጣት በባህርዳር ማክበሩ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment