FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, January 22, 2013

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቀ


ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በኢትዮጵያና በዛምቢያ መካከል  ትናንት ምሽት የተደረገውን እግር ኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  ከማሰራጫ ቻናል በድብቅ በመውሰድ ማስተላለፉን ደርሼበታለሁ ሲል የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) መግለጹን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ዘገበ
እንደ ዘገባው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሌሎች የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያሰራጩትን ጨዋታ በመስረቅ ጨዋታውን እንዳስተላለፈ የተደረሰበት በእረፍት ሰዓት የጨዋታው ስፖንሰር እንደሆኑ አድርጎ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሲሰራ ነው።
በካፍ መግለጫ መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፈጸመው ማጭበርበር ሁለት መልክ ያለው ነው።
አንዱ ማጭበርበር ጨዋታውን ክፍያ ሳይፈጽም በድብቅ ማስተላለፉ ሲሆን፤ሁለተኛው ደግሞ በዚያው በተሰረቀ የአየር ሰዓት "ይህን ጨዋታ  ስፖንሰር በመሆን ያስተላለፉላችሁ እነ እገሌ ናቸው” እያለ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ መሥራቱ ነው።
ይህ የኢቲቪ ድርጊትም በሁለተኛው ግማሽ  በጨዋታው ኮሜንታተር ሁለት ጊዜ ተጋልጧል እንደ ጋዜጣው ዘገባ ።
ጨዋታውን ለማስተላለፍ ፈቃድ ያለው የቴሌቪዥን ጣቢያም በጨዋታው መሀል በፃፈው "ቴክስት" የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ድርጅት ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይፈጽም ጨዋታውን  እያስተላለፈ ነው።" በማለት ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ 31 ዓመት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ቢያልፍም፤ መንግስት ለቴሌቪዥን ስርጭት ከፍተኛ ገንዘብ ተጠይቄያለሁ፤ ይህም ዋጋ በጣም ተወዶብኛል" በማለት ላለማስተላለፍ መወሰኑ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ በዘርፈ-ብዙ ሙስና በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ብር የሚዘረፍባትና ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች ሳይቀሩ በሆነ ባልሆነው  ከፍተኛ ገንዘብ የሚያፈሱባት አገር መሆኗን የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ቀደም ካሉት ቀናት አንስቶ አስተያየት ሲሰጡ የነበሩ ሰዎች፡ "18 ሚሊዮን ብር እንኳን ለመንግስት ለዘመኑ ባለሀብቶች ቀላል ነው፤ በዚያ ላይ ሁሉንም ባይሆን የተወሰነውን ከአገር ውስጥ ማስታወቂያ መሸፈን ይቻላል። መንግስት ማሳየት ያልፈለገው በእርግጥ ገንዘብ አጥቶ ነው? ወይስ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄድን ተቃውሞ በመፍራት ነው?"በማለት ሲጠይቁ ነበር።
ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ የተመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን፦"በልጆቻችን በኮራንበት ቀን ለማይረባ ገንዘብ  ሲል ተራ ማጭበርበር ውስጥ በገባው መንግስት አፈርን፤ ግለሰብ ቢሰርቅ በህግ ይጠየቅ እንል ነበር። የሰረቀው "ሌባ መቀጣት አለበት" የሚል ህግ የፃፈው መንግስት ነው ሲባል ግን ከማፈር በስተቀር ምን እንላለን?" ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም። 

No comments:

Post a Comment