FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, January 22, 2013

“በአስመራ ሁሉም ነገር የተረጋጋ ነው” ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ተናገሩ


ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- አቶ የማነ ገብረመስቀል ለኤኤፍ ፒ  አስመራ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም የተረጋጋች ናት በማለት ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ሳሊህ ኦማር በበኩላቸው ምንም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራም ሆነ ምንም አይነት የአመጽ እንቅስቃሴ  አልታየም ብለዋል።
ቢቢሲ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ የማስታወቂያ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት አማጺዎች፣ መስሪያ ቤቱን ለቀው ወጥተዋል። ተቋርጦ የነበረው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ስርጭቱን መጀመሩንም ገልጿል።
ኢሳት ከትናንት ጀምሮ አስመራ በመደወል ጉዳዩን ለማጣራት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም፤ ይሁን እንጅ በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ” ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ አለማየታቸውን፣ ጉዳያቸውን ያለምንም ችግር ሲያከናውኑ መዋላቸውን” ገልጸዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ኢትዮጵያዊ “ከአገሪቱ ቴሌቪዥን  መጥፋት በስተቀር፣ ስልኮች አለመቋረጣቸውን፣ ታክሲዎች ያለምንም ችግር አግልግሎት ሲሰጡ እንደነበር፣ ሱቆችም ተከፍተው መዋላቸውን፣ እንዲሁም የተኩስ ድምጽ አለመስማቱንም” ገልጿል”
የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን በመግለጽ ዘገባዎችን ማሰራጨታቸው ይታወሳል። 

No comments:

Post a Comment