FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 30, 2013

የአቶ ጁነዲን ያለመከሰሰ መብት ያለመነሳት ጉዳይ ማነጋገሩን ቀጥሏል


ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት በአጀንዳ መልክ ለፓርላማ ቀርቦ
የነበረውና ባልታወቀ ምክንያት ፓርላማው እንዳይወያይበት በተደረገው የቀድሞ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ
አባልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ ሕግ አስፈጻሚው አካል አሁንም ዝምታን መምረጡ
አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል፡፡

ፓርላማው ከሁለት ሳምንት በፊት ባቀረበው አጀንዳ የአንድ የም/ቤት አባል ያለመከሰሰ መብት ስለማንሳት
በሚል ለውይይት አጀንዳ መያዙን ካስታወቀ በኃላ በድንገት ስብሰባው ከተጀመረ በሁዋላ ለሌላ ጊዜ
መተላለፉ በአፈጉባዔው በኩል ተገልጾአል፡፡

የፓርላማው ምንጮች እንደገለጹት አጀንዳው በፓርላማው ከኦሮሚያ ደራ ወረዳ ተመራጭ የሆኑትን አቶ
ጁነዲን ሳዶን የሚመለከት ነበር፡፡

ሆኖም ባልታወቀ ምክንያት አጀንዳው እንዲያድር ከተደረገ በኋላ ላለፉት አስራአምስት ቀናት
በላይ ዝምታ መመረጡ የብዙዎችን ትኩረት መሳቡ ታውቋል፡፡

አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤታቸው / ሐቢባ መሐመድ አዲስ አበባ ከሚገኘው ሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና የተለያዩ
መጽሐፍትን ተረክበው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ከተያዙበት ከሐምሌ 9 ቀን 2004 . ጀምሮ ከመንግስታዊ
ኃላፊነታቸው በተጨማሪ በመስከረም ወር መጨረሻ የዓመቱ መደበኛ ሥራውን የጀመረው ፓርላማ ተገኝተው
አያውቁም፡፡

ከባለቤታቸው ጥፋት ጋር ተያይዞ ከኦህዴድ አመራርነት ተገምግመው እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን
በጠ/ሚ ኃይለማርያም አዲሱ ካቢኔም ተወግደው በአቶ ሙክታር ከድር መተካታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባለቤታቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክሳቸውን እየተከታተሉ ቢሆንም ከሳዑዲ ኤምባሲ ጋር ከነበራቸው
ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሟች እናታቸውን ኑዛዜ ለማስፈጸም የገንዘብ ዕርዳታ የጠየቁት ራሳቸው መሆናቸውን
በመግለጽ ባለቤታቸው በጉዳዩ እጃቸው እንደሌለበት በይፋ ቢናገሩም እስካሁን የተጠየቁበት ሁኔታ አለመኖሩ
የህግ ሥርዓቱን ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል፡፡

ፓርላማው ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት ያደረገው ሙከራም የከሸፈበት ምክንያትም ለብዙዎች
እንቆቅልሽ እንደሆነ ነው፡፡ በተያያዘም ነሐሴ 14 ቀን 2004 . ባለቤታቸውን አቶ መለስ ዜናዊን
በድንገተኛ በሞት ያጡት / አዜብ መስፍን ከሐዘናቸው ካገገሙም በኋላ በፓርላማ ውስጥ ተገኝተው
እንደማያውቁ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ፓርላማው 3 ዓመት የስራ ዘመኑን በመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን መደበኛ ስብሰባዎችን
እያስተጓጎለም ቢሆን 15 መደበኛ ስብሰባዎችን ያካሄደ ቢሆንም የፓርላማው አባል የሆኑት / አዜብ
በአንዱም ስብሰባ ላይ አልታዩም፡፡

እንደ  ምንጮቻችን ገለፃ አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በቁም የተነሱትን ፎቶግራፍ ሁሉም
አባላት ሊያዩት በሚችሉበት ሁኔታ ፊት ለፊት የተሰቀለ ሲሆን ይህ ፎቶ በትልቁ ፊት ለፊት መሰቀሉ በብዙዎቹ
የፖርላማ  አባለት ዘንድ አሁንም ፖርላማውን እየመሩ ያሉት እርሳቸው እንደሆኑ የሚያሳስብ መንፈስ
ፈጥሮባቸዋል::


No comments:

Post a Comment