FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, January 26, 2013

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዋሊያዎች ጎን እስከመጨረሻው እንደሚቆሙ ገለጹ


ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ያነጋገራቸው ደጋፊዎች እንዳሉት ምንም እንኳ ብሄራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በተጫወተበት እለት ያገኘው ውጤት  አሳዛኝ ቢሆንም፣ በቀጣዩ ጨዋታ የናይጀሪያን ቡድን በማሸነፍ ለቀጣዩ ዙር ለማለፍ ድጋፋቸውን አጠንከረው እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚኖረው ደጀኑ በቀለ ድሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚሆን ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል
ከቡርኪና ፋሶ ከነበረው ጨዋታ በፊት ኢትዮጵያውያን ኮከብ ካለው ሰንደቃላማዎች ውጭ ሌሎችን ሰንደቃላማዎችን ይዘው ወደ ሜደ እንዳይገቡ ተከልክለው እንደነበር ታውቋል።
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን መንግስት እግርኳስ ጨዋታውን ለፖለቲካ አላማ ለማዋል ሞክረዋል በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
በሌላ በኩል በዚህን ያህል የጎል ልዩነት እንሸነፋለን ብለን አልጠበቅንም ያሉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው፤ ለዚህ የዳረገን ዋነኛው ችግር ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን በጉዳት ሳቢያ ማጣታችን ነው ብለዋል።
“በብሔራዊ ቡድናችን ውጤት እጅግ ብናዝንም፤ ነገም ሌላ ቀን ነውና እንደሚክሱን እናምናለን፤ ተስፋ አንቆርጥም።

No comments:

Post a Comment