FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, January 1, 2013

ወያኔን ውሃ ሲወስደው ምራቅህን እንትፍ ብለህ ጨምርበት !


ወያኔን እና ባንዳዎቹን ወሃ ሲወስዳቸው ምራቅህን እንትፍ ብለህ ጨምርበት በሚል ርዕስ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር ያዘጋጀው አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ ማምሻውን ተጠናቀቀ።
ሰሞኑንን በአሸባሪው የወያኔ ስረአት ላይ የትጥቅ ትግል በጀመረው የግቦት 7 ሐይል ላይ የማጥላላት ዘመቻ የከፈቱ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ተቆጥበው የህዝብን ትግል መቀላቀል እንደሚገባቸው በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር አባላት አሳሰቡ።
በዋንኛነት በአባላት መሃከል አከራካሪ የነበረው የግንቦት 7 ሃይል የትጥቅ ትግል መጀመርን ተከትሎ ቀደም ሲል ክቡር አቶ ብረሃኑ ነጋ ለኢሳት የሰጡት መግለጫ በህብረተሰቡ ውስጥ ብዥታ መፍጠሩን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ሰሞኑንን አንዳንድ ግለሰቦች በወያኔ ላይ የተጀመረውን ሃገር አቀፋዊ ትግል ለማደብዘዝ ሲራወጡ መታየታቸው አግባብነት የሌለው መሆኑንን ወጣቶቹ በመግለጽ ድርጊቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቆሚያለው ከሚል ወገን የማይጠበቅ እና አሳፋሪ በመሆኑ ግለሰቦቹ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንደሚገባቸው በአንድ ድምጽ የጋራ አቋማቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ ባሻገር ወጣቶቹ ዛሬ ባደረጉት አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ ላይ በዋንኛነት ከያዟቸው አጀንዳዎቻቸው ውስጥ፡ግንባር ቀደም እና አንዱ በሆነው ሰሞኑንን በሪያድ መንፉሃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በብሄር ጉሩፕ ፈጠረው በሚፈጽሙት የእርስ በርስ ግጭት በሃገራችን በጎ ገጽታ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ግምት ውስጥ፡በማስገባት እና አንዳንድ ወገኖች ባለማወቅ ርካሽ በሆነ ወያኔያዊ የብሄር አስተሳሰብ ተበርዘው በሰው ሃገር በሚፈጽሙት ዘግናኝ ድርጊት በሳንጃ ታርዶ እንደወጣ የሚቀረውን ኢትዮጵያዊ ወጣት ህይወት ከወዲሁ ለመታደግ በዚህ ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ወጣቶች ለሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች መረጃ በመስጠት ከአካባቢው ህበረተሰብ እና ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚሉ ማናቸውም አካላት ጋር በመተባበር ስረአት አልበኛ የሆኑ ወገኖቻችንን አጋልጦ ለመስጠት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
ከዚህ ባሻገር የፊታችን አርብ ታህሳስ 26 ቀን 2005 የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ከመንግስት አንጻር ለሃይማኖታቸው ነጻነት መከበር ትግል የጀመሩበትን 1 አመት አስመልክቶ በመላው አለም የተጠራው ታላቅ የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ተቃውሞ ማገዝ የሚያስችሉ የተለያዩ የትግል ስልቶችን የወጣት ማህበሩ መቀየሱን እና ለዚህም ትግል መሳካት ወጣቱ በሪያድ የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር የበለጠ በቅርበት ለመስራት ወስነዋል።
ወያኔን ውሃ ሲወስደው ምራቅህን እንትፍ ብለህ ጨምርበት !!!
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር

No comments:

Post a Comment