ዓለም ባንክ ቴሌን ዳር ዳር እያለው ነው!
የዓለም ባንክ ባለፈው ዓርብ ይፋ ባደረገው ጥናት የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ ሙስና አደጋ የተጋለጠ መሆኑን ሲያረጋግጥ፣ በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሒደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል ተብሏል፡፡
መንግሥት ከባንኩ ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት የባንኩ አጥኚ ቡድን የአገሪቱን የሙስና መጠን ለስድስት ወራት ያህል ሲያጠና ቆይቷል፡፡ ጥናቱ የተካሄደባቸው ስምንት ዋና ዋና ዘርፎች ሲሆኑ፣ በአብዛኞቹ ዘርፎች ላይ የሙስና መንሰራፋት ያን ያህል አሳሳቢ በሚባል ደረጃ ላይ አይደለም ብሏል፡፡ ሆኖም ጥናቱ “አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎች” ብሎ በመደባቸው ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ የተካተቱት ቴሌኮም፣ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና ሕክምና እንዲሁም የመድኃኒት ዘርፉ በሙስና ቀለበት ውስጥ የወደቁ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡
ጥናቱ በአጠቃላይ የአገሪቱን ስምንት ዋና ዋና ዘርፎች በሦስት ክፍሎች መድቧቸዋል፡፡ “የመሠረታዊ አገልግሎት ሰጭ ዘርፎች”፣ “አሮጌዎቹ ዘርፎች”፣ እንዲሁም “አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎች” በማለት የመደባቸው ሲሆን፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ውስጥ የተካተቱት፣ ከፍተኛ ፈንድ የሚጎርፍላቸው ከመሆናቸው ባሻገር ከሌሎቹ ዘርፎች አኳያ በአገሪቱ ያላቸው ተሞክሮ አነስተኛ ሆኖ የሚገኙ ናቸው፡፡
በመሠረታዊ የአገልግሎት ሰጭ ዘርፍ ውስጥ የተካተቱት እንደጤና፣ ትምህርት፣ ፍትሕና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በአሮጌው ዘርፍ ውስጥ ደግሞ እንደ ማዕድን፣ ኮንስትራክሽን፣ መሬትና ሌሎችም ተደልድለዋል፡፡
የባንኩ የጥናት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት፣ በመሠረታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማቱም ሆነ በአሮጌዎቹ ዘንድ የሚታየው የሙስና ደረጃ ያን ያህል አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ አይደለም፡፡ ምንም እንኳ በዘርፎቹ የሚታየው የሙስና መጠን እያደገ ቢመጣም፣ ህልውናቸውን እንደማይፈታተነው ጥናቱ አመላክቷል፡፡ በተለይ የመሠረታዊ አገልግሎት ዘርፉ ከሌሎቹ አኳያ ለሙስና ያለው ተጋላጭነት አነስተኛ ሆኖ ይታያል፡፡
ከዚህ ይልቅ አሮጌዎቹ ዘርፎች ለሙስና ያላቸው አስተዋጽኦ ከአዳዲሶቹ ቀጥሎ ያስቀምጣቸዋል፡፡ በተለይ የቴሌኮም ዘርፉን በመከተል መሬትና ኮንስትራክሽን በሙስና አደጋ ውስጥ ቢገኙም፣ የትኞቹም የቴሌኮም ዘርፉን ያህል ግን አይደሉም፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት “ቴሌን ደህና ሰንብት?” በሚል ርዕስ ባወጣነው ዜና ላይ ቴሌ የአውሮጳውያንን ኩባንያዎች ማግለሉና በሙስና የተዘፈቀ ድርጅት መሆኑ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ (ከላይ የተጠናቀረውን ዜና በቀጥታ የወሰድነው ከሪፖርተር ነው)

No comments:
Post a Comment