FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 2, 2013

በኩዌት አንድ ኢትዮጵያዊት ሞታ ተገኘች / በተውለደሬ ወረዳ አንድ ጠበቃ በክርክር በማሸነፋቸው በቀበሌው ባለስልጣናት ተደበደቡ


በኩዌት አንድ ኢትዮጵያዊት ሞታ ተገኘች
ታህሳስ  ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አረብ ታይምስ እንደዘገበው ኢትዮጵያዊቷ የሞተቸው ከቀጣሪዋ ድርጅት መስኮት ላይ ዘላ በመውደቅ ሳይሆን አይቀርም።
ሰራተኛዋ በራስ ቅሏ አካባቢ ከፍተኛ ደም ፈሷት እንደሞተች የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል።
በግቢው ውስጥ ሌሎች ሶስት ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች እንደነበሩ ቢገለጽም ኢትዮጵያውያኑ የቤት ሰራተኛዋ በምን ሰበብ እራሱዋን እንዳጠፋች እንደማያውቁ ገልጸዋል።


በተውለደሬ ወረዳ አንድ ጠበቃ በክርክር በማሸነፋቸው በቀበሌው ባለስልጣናት ተደበደቡ

ታህሳስ  ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ በተውለደሬ ወረዳ አቶ አበራ ካሳ የተባሉ ጠበቃ ከቀበሌው ሊቀመንበር ጋር በመሬት ጉዳይ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ክርክር በፍርድ ቤት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ፣ ሊቀመንበሩ ደጋፊዎቻቸውን አስተባብረው ጠበቃው እንዲደበደቡ አድርገዋል፡፡ ጠበቃውም  በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ሆስፒታል ገብተዋል።
የመሬቱ ባለቤት አቶ አስፋው ሽበሺ የሚባሉ አርሶአደር ሲሆኑ ፣ የቀበሌው 01 እና 02 ሊቀመንበሮች መሬቱን ለግላቸው ለማድረግ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርጉ ነበር።
የቀበሌ ሊቀመንበሮቹ ትናንት ምሽት ላይ የአርሶአደር ሽበሺን ቤት ያቃጠሉባቸው ሲሆን፣ የጠበቃው ባለቤት ደግሞ ዛሬ ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ ቤታቸው እንደሚቃጠልባቸው ተነግሮአቸው ቤታቸውን መልቀቃቸው ታውቋል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ በተወልደሬ ወረዳ የቀበሌ ባለስልጣናቱ መንግስት እንደሌለ አድርገው እንደሚቆጥሩና ህብረተሰቡን እንደሚያሰቃዩ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment