FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, January 3, 2013

በመቀሌ ከተማ የግል ጋዜጣና መጽሄት አዞሪዎችና ሻጮች ስራቸው ህገወጥ በመሆኑ ከስራ መታገዳቸው ተገለጠ


ታህሳስ  ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በከተማዋ በቋሚነት ደርድረውና እያዞሩ ጋዜጣና መጽሄት የሚሸጡ በመከልከላቸው ህዝቡ ጋዜጣ ማግኘት አለመቻሉን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችና የቅርብ ምንጮች ያላቸውን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል::
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁና በአካባቢው ጋዜጣና መጽሄት በመሸጥ የሚተዳደሩ ወጣቶች የጠቀሰው ዘገባ የከተማዋ ወያኔ ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ አስተዳደር ስራው ህገወጥ መሆኑ ተገልፆላቸው ከታህሳስ 5፣2005 ጀምሮ በአካባቢው የግል ጋዜጣና መጽሄት የመሸጥ ስራ እንዳይሰራ መታገዱን አመልክቷል::
ይህንን ትእዛዝ ተላልፋችሁ ጋዜጣና መጽሄት እያዞራችሁ ተገኝታችኋል የተባሉ አምስት ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው የታወቀ ሲሆን ሲያዞሩት የነበረው ጋዜጣና መጽሄት መወረሱ ተዘግቧል::

No comments:

Post a Comment