ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከስፍራው የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሱሪዎችን የቤት እንስሶቻቸውን በመውሰድ የአካባቢውን ህዝብ በግድ ወደ ሰፈራ ጣቢያ ለማንቀሳቀስ ባደረጉት ሙከራ ነው ዲማ በሚባለው አካባቢ የተኩስ ልውውጥ የተደረገው።
በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ለማወቅ አልተቻለም።
ኢሳት ባለፈው ሳምንት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ150 በላይ ሱሪዎች መገደላቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ጉባኤ ተደናቀፈ
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሊያካሂዱት የነበረው አመታዊ ጉባኤ ገዢው ፓርቲ አስርጎ ባስገባቸው ወጣቶች መደናቀፉን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል።
በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎች ለማህበሩ አዳራሽ ለማከራየት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶቹ ጉባኤያቸውን በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ውስጥ ለማካሄድ ተገደው ነበር።
ይሁን እንጅ ዛሬ ጧት ስብሰባው በሚካሄድበት ወቅት የተወሰኑ ወጣቶች ስብሰባውን ማደናቀፋቸውንና ይህንኑ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስፍራው በፍጥነት በመምጣት 6 የአመራር አባላትን ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ቀኑን ሙሉ ካሰሩዋቸው በሁዋላ በዋስ እንደለቀቁዋቸው የወጣቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ሚካኤል ተናግሯል።
No comments:
Post a Comment