FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, January 11, 2013

የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። / አርቲስቶች በየካቲት ወር ለሚከበረው የመከላከያ ቀን ቅስቀሳ ጀመሩ


ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ባሳላፍነው ወር የነበረው የዋጋ ግሽበት ወደ 12 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱን የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። አሀዙ ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በ1 ነጥብ ሁለት መቀነሱን ኤጀንሲው አስታውቋል። ይሁን እንጅ በምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ አሳይቷል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ8 ወራት በፊት ሰኔ ወር ላይ ባደረጉት ንግግር የዋጋ ንረቱን ወደ አንድ አሀዝ እንደሚያወርዱት ተናግረው ነበር። በመስከረም ወር ላይ ግሽበቱ ቅናሽ ሊያሳይ አልቻለም ነበር። ባሳለፍነው ወር  በእህል ምርቶች ላይ የታየው መጠነኛ ቅናሽ መንግስት ስንዴ በገፍ ከውጭ አገር በማስመጣቱ የተገኘ ነው። በየትኛውም መመዘኛ 13 በመቶ የዋጋ ግሽበት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ በዋጋ ንረቱ የተነሳ ኑሮውን ለመቋቋም እንዳላስቻለው በተደጋጋሚ በኢሳትና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል።



አርቲስቶች በየካቲት ወር ለሚከበረው የመከላከያ ቀን ቅስቀሳ ጀመሩ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬና ሙሉአለም ታደሰ የሚመራው ግብረሀይል ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከቲያትሪካል አርት ተማሪዎች ገር ተገናኝቶ ስለመከላከያ ቀን አከባበር ውይይት ማድረጉ ታውቋል።
የኔነሽ ወልደገብሬልና ሌሎችም አርቲስቶች በስፍራው መገኘታቸውን የዩኒቨርስቲ ዘጋቢያችን ገልጿል።
አርቲስቶች በቅርቡ የአትዮጵያ አየር ሀይልን ጨምሮ የመከላከያን ኢንጂነሪንግን እንዲጎበኙ መደረጋቸው ይታወቃል። የጉብኝቱ አላማ አርቲስቶቹ በመጪው የመከላካያ ቀን በአል አከባበር ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ታስቦ የተደረገ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ከ98 በመቶ በላይ በአንድ ብሄር አመራር ስር እንዲሆን ተደርጎ መዋቀሩ በእየአቅጣጫው ተቃውሞ ትችት እያስነሳ እንደሚገኝ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment