FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 16, 2013

የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ / የዩናይትድ ስቴት የሴኔት ኣባላቶችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን ደቡብ ሱዳን ነዳጇን በኢትዮጵያ በኩል ለተቀሪው አለም አንድትልክ ፕሬዝዳንቱን ሳልሻ ኬርን አስጠነቀቁ


ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥ ኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የእስር ፍርድ ወስነውበታል::
በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎች እንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበት ተወስኖባቸዋል::
 የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለው የሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙን ማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነው ይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደ ሱማሊያ ዳግም መዝመቱንም አስታውሷል::


የዩናይትድ ስቴት የሴኔት ኣባላቶችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን ደቡብ ሱዳን ነዳጇን በኢትዮጵያ በኩል ለተቀሪው ኣለም አንድትልክ ፕሬዝዳንቱን ሳልሻ ኬርን አስጠነቀቁ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ሱዳን ትሪቡንን ዋቢ ያደረገው ኦል ኣፍሪካ እንደዘገበው የሴኔቱ ኣባላቶች የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬርን ነዳጃቸውን ለአለም ገበያ ለማቅረብ ካርቱምን መጠቀምና መጠበቅ እንደሌለባቸው አሳስበዋል::
ባለፈው አመት ግንቦት ወር የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ሚኒስቴር ስቲፍን ዶ ለዎልስትሪት ጆርናል እንደገለጹት ቢያንስ ቢያንስ የነዳጅ ምርታቸውን 10 በመቶ ወይም ሰላሳ አምስት ሺ በርሜል በቀን በከባድ መኪና (በቦቴ) ኢትዮጵያንና ኬንያን አቆራርጠው በጅቡቲ ለአለም ገበያ ለማቅረብ አቅደዋል::
በዚህ ሳምንት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን የጎበኙት የአሜሪካ የሴኔት አባላቶች የሰሜን ሱዳን የነዳጅ ዘይት ማጓጓዝን የማስ ፉከራ ትርጉም የለውም ካሉ በኋላ ነዳጃቸውን ለአለም ገበያ ለማቅረብ ከባድ መኪናንና ኢትዮጵያን መጠቀም አለባቸው ሲሉ አስታውቀዋል::

No comments:

Post a Comment