FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 16, 2013

በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ / በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ማህበሩን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚመሩ 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡን አስታወቀ


ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6 ከመቶ ደኗን አታለች::
በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል::
ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና እንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል::
በኢትዮጵያ በደን የተሸፈኑ መሬቶች ተጨፍጭፈው በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል::



በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ማህበሩን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚመሩ 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡን አስታወቀ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዚህ መሰረት ማህበሩ ከተቋቋመበት ጀምሮ ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት በመሩት በዶ/ር ሼክስፔር ፈይሳ ምትክ አቶ አበበ ሀይሉ ም/ፕሬዚዳንት ደግሞ ዶ/ር ሰለሞን ረታ አድርጎ ሠይሟል::
በተዋረድ በዋና ጸሀፊነት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በፋይናንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንትና በመድረክ አስተባባሪነት በቀድሞ የስራ አስፈጻሚዎች ምትክ አዲስ ተመርጧል::
የቀድሞ የማህበሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ለአዲሶቹ ተመራጮች የስራና የንብረት ርክክብ የፈጸሙ መሆኑን የገለጠው የማህበሩ መግለጫ የኢትዮጵያውያን ማህበራት፣ ተባባሪ አባላት፣ የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲዎች ለአዲሱ አመራር የተለመደ የስራ ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጠይቋል::
ማህበሩ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው በዚህ መግለጫ የአድዋን ድል አስመልክቶ በማርች ሁለት ለሚኖረው ዝግጅት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በዋሽንግተን ዲሲም ሶስተኛው ፊስቲቫል በሳምር እንደሚካሄድ አስታውቆል::
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር የኢትዮጵያን ቅርሶችና ታሪኳን መጠበቅና ማስተዋወቅ ከአላማዎቹ በዋናነት ይዞ ለተግባራዊነቱ የሚንቀሳቀስ ድርግት መሆኑ ይታወቃል::

No comments:

Post a Comment