FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, January 15, 2013

በመከላከያ ሰራዊትና በሱሪዎች መካከል የተካሄደው ግጭት ቀጥሎ 3 ሱሪዎች መገደላቸው ታወቀ / 20 የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም እንደታሰሩ ነው


ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በሱሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተነሳ ግጭት 3 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል።
በግጭቱ በርካታ የሱሪ ከብቶች መገደላቸውን ለማወቅ  ተችሎአል።
ባለፈው ቅዳሜ በአካባቢው ግጭት ተነስቶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።
መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።


20 የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም እንደታሰሩ ነው

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በቅርቡ በድሬዳዋ ከምግብ ጋር በተያያዘ ተነስቶ በነበረው ግጭት ታስረው ከነበሩት መካከል 300 የሚሆኑት ሲፈቱ አሁንም 20 ተማሪዎች ታስረዋል።
የዩኒቨርስቲው ምንጮች እንደገለጡት የፌደራል ፖሊስ አባላት በጊዜው በተማሪዎች ላይ ካደረሱት ከፍተኛ ድብደባ በተጨማሪ የተማሪዎችን ሞባይሎች ሳይቀር መውሰዳቸው ታውቋል።
በእለቱ በተፈጠረው ችግር ግምቱ ከ150 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወድሟል።
የግጭቱ መንስኤ ከምግብ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ የዩኒቨርስቲው ምንጮች እንደሚሉት የዩኒቨርስቲው ዲን ባለፈው አመት 17 ሚሊዮን ብር ከምግብ ወጪ ቀንሰው ተመላሽ በማድረጋቸው መሸለማቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment