FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, January 1, 2013

ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ቡራኬ ሰጡ፤ ሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ አስጠነቀቁ


Abuna Merkorios (Patriarch and Catholicos of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church)
ትናንት እሁድ ታህሳስ 21 ቀን በቶሮንቶ በተከበረው አመታዊው የታህሳስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ላይ ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ለህዝቡ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን፤ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ከሰላምና አንድነት ሂደቱ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ አሳዛኝ አቅጣጫ እየያዘ መሆኑን ገልጸው፤ ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ ህዝቡ በንቃት እንዲጠባበቅ አሳስበዋል።
በትናንትናው እለት በተከበረውን የታህሳስ ገብርኤል በል ላይ ለህዝቡ ባሰሙት አጭር የመግቢያ ንግግር፤ የውጪው ሲኖዶስ አባላት የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲከበር ጥረት ቢያደርጉም፤ ከሰላምና አንድነት ጉባኤው አዘጋጆቹ አንዱና የኢትዮጵያውን ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያናግሩ ሄደው የነበሩት ሊቀካህናት ሀይለስላሴ አለማየሁ ከቤታቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው በአጃቢ ወደአሜሪካ በግድ እንዲመለሱ እንደተደረጉ ተናግረዋል።
ሌላኛው ሸምጋይ ዲያቆን አንዱአለም የደረሰበት እንደማይታወቅም ተናግረው ዝርዝሩን በመጪው ሳምንት ለህዝቡ እንደሚገልጹና ህዝቡም በንቃት እንዲከታተል አሳስበዋል።
በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በዚህ ሳምንት የጉዳዩን መጨረሻ ተመልከተው ስለሰላምና አንድነት ሂደቱና በሸምጋዮቹ ላይ ስለደረሰው ችግር መግለጫ እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።
በትናንትናው እለት በተከበረው በዓል ላይ ባለፈው ወር የቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ካቴድራልን መርቀው የከፈቱት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትሪያርክ ርእሰ ልቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የተገኙ ሲሆን፤ የአቋቀም ሊቅ የሆኑት ፓትሪያርክ በእለቱ በቅዳሴና በዝማሬ፤ በብርቱ መንፈስ ሲያገለግሉ ውለዋል።
የፓትሪያርኩ ጤናም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
source: www.ecadforum.com

No comments:

Post a Comment